The New Church Project Addis abeba
Comments Off
|
|
|
|||||||||||||||||
የኮንፈረስ ማስታወቂያየኮንፈረስ ማስታወቂያየዘንድሮው የአውሮፓ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ኮንፈረስ በጀርመን ሀገር በሃኖቨር ከተማ ከ ነሃሴ 6 እስከ 8 2003 (12/08/2011 እስከ 14/08/2011 እ.ኤ.አ.) ይካሄዳሌ። ሀ. የኮንፈረሱ አዳራሽ ያለበት ሥፍራ፤የኮንፈረሱ አዳራሽ ያለበት ቦታ “ስቴፋንስ ስቲፍት ኮንፈረንስ ማዕከል” ይባላል። የሥፍራው ሙሉ አድራሻ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ነው። STEPHANSSTIFT educational, study and meeting centre Kirchröder Straße 44, D-30625 Hannover, Germany የተከራየነው አዳራሽ የተሟላ ሆኖ እስከ 250 ሰው ሊይዝ የሚችል ነው። ለ. ምግብና መኝታበ “ሀ” የተጠቀሰው ማዕከሌ እስከ 10/07/2011 ባለው ጊዜ ውስጥ ሊሚመዘገቡ ሰዎች የተሟላ አገልግሎት ማለትም ምግብና አልጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሰጠናል። ለዚህ ጉዳይ እባክዎ ወንድም ደጀኔን ያነጋግሩ። የግዜውን ነገር ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈሌጋል። (dejene_eticha@yahoo.com) 00 49 5113739752 የሆቴሉ ዋጋ ከነምግቡ በቀን እና በሰው ቁጥር፦ ለነጠላ አልጋ (Single bed room) – በቀን 67 ኤይሮ ለአንድ ሰው ከነምግቡ (ቁርስ ምሳ እና እራት) ለሁለት ሰው አልጋ (Double bed room) – በቀን 55 ኤይሮ ለአንድ ሰው ከነምግቡ (ቁርስ ምሳ እና እራት)፣ ለሁለቱ 110 ኤይሮ ማለት ነው። ሐ. የምግብ ሰዓታትከላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቦታ ሆቴል ስለአይደለ፣ የምግብ ሰዓትን የመጠበቅና በግዜ የማሳወቅ ታማኝነት ከኛ ይጠበቅብናል። ቁርስ – 8.00 ሰአት የምግብ ዋጋ ከሆቴሉ ዋጋ ጋር ተጠቃሎአል። እነዚህ የምግብ ሰዓቶች ከላይ የተጠቀሰው ቦታ ለሚያድሩ እንግዶች ብቻ ነው። ማዕከሉ ሌላ ቦታ ለሚያርፉ እንግዶች የምግብ አገልግሎት አይሰጥም። መ. ወደ ኮንፈረንሱ አዳራሽ ለመምጣት የሚረዳ መረጃ፦ከሃኖቨር ባቡር ጣቢያ ለሚነሱ፦ የከተማ ባቡር (ትራም) ቁጥር 1 ወደ Laatzen/Sarstedt አቅጣጫ የሚሄድ፣ ወይም ቁጥር 2 ወደ Rethen አቅጣጫ የሚሄድ፣ አሌያም ቁጥር 8 ወደ Messe/Nord አቅጣጫ የሚሄድ፣ ከሶስቱ አንዱን በመውሰድ፡ ከሁለት ማቆሚያ በኃላ Aegidientorplatz ይውረዱ። ከዚያም ትራም ቁጥር 4 ወደ Roderbruch አቅጣጫ የሚሄድ፣ ወይም ቁጥር 5 ወደ Anderten አቅጣጫ የሚሄድ ተሳፍረው Nackenberg/Stephansstift ይወርዳለ። የኮንፈረንሱ አዳራሽ ያለበት ጊቢ ከባቡር ማቆሚያው አጠገብ በቀኝ በኩል ይገኛል ። እዚህ ቦታ ለመድረስ የሚያስፈልግ ትኬት ከባቡር ጣቢያው አውቶማት ለዞን አንድ ብለው ይግዙ። ዋጋው 2.30 ኤይሮ ነው። ከሃኖቨር አውሮፕሊን ማረፍያ ለሚነሱ፦ ከአውሮፕሊን ማረፍያ ወደ ባቡር ጣቢያ የሚሄድ ባቡር በየ 30 ደቂቃ አለ። ይህንን ባቡር ይዘው ወደ ባቡር ጣቢያ ይደርሱ እና ከባቡር ጣቢያ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው መልክ ወደ ኮንፈረንሱ አዳራሽ መምጣት ይችላሉ። ከአውሮፕላን ማረፍያ ወደ ባቡር ጣቢያ ለመድረስ 17 ደቂቃ ይወስዳል። የትኬት ዋጋ 3 ኤይሮ ነው። ለዚህ ዞን 2 ብለው ከቲኬት አውቶማት ይግዙ። ረ. ከላይ የተጠቀሰው ቦታ ለማያርፉ ሰዎችእስከ 10/07/2011 ባለው ጊዜ ውስጥ ያልተመዘገቡ ሰዎች፣ ማደሪያ ሆቴሌ በራሳቸው መንገድ መፈለግ ይጠበቅባቸዋሌ። ለዚህ እንደ አማራጭ ከታች ያለውን ሊንክ ማየት ይችሊለ። GHotel (ከኮንፈረሱ ቦታ 15-20 ደቂቃ በእግር ያስኬዳሌ) ETAP Hotel (ከኮንፈረሱ ቦታ 15 ደቂቃ በትራም ያስኬዳሌ) |
|||||||||||||||||||
| /**/ | |||||||||||||||||||
| HOME Doctrin Amharic Doctrin Engilish |
Tracts Video Youtube Video Prechings Photographs Audio Song Audio Sermon |
Amharic Bible English Bible Amharic SERA |
Amharic tracts English Tracts Amharic Articls on topic Articles on Topiic Books Jornals |
Forum Blogs |
Contact Help paltalk how |