|
||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ
መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ቦታ እንኳን ከአንድ በላይ አምላክ እንዳለ አይናገርም። መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት መጽሐፍ ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ የሚያስተምረው በሙሉ ኢግዚአብሐር አንድ ብቻ እንደሆነ ነው። በዘዳ 6፡4 እንደተጻፈው ፊተኛይቱ ትእዛዝ እግዚአብሔር አንድ ነው የምትል ናት ማር.12፡29_30። በኢሳ.44.24_25 እንደተጻፈው ከአንዱ አምለክ ጋር ሌላ አምላክ ስይኖር አንዱ ሁሉን ለብቻው እንደፈጠረ ይናገራል። በኢሳ. 40፡12_14 እንደተጻፈው ፍጥረትን ሁሉ ሲፈጥር አማካሪ ወይም የተርመካከረው ሌላ መሰል አምላክ አልነበረም። በኢሳ.44፡8 ኢንደተጻፈው እግዚአብሔር ሌላ አምላክ እንደማያውቅ ት4አናግሯል። በዘካ.14፡5_9 እንደተጻፈው የሚመጣውና ሁሉን የሚገዛ የነገሥታት ንጉሥና የገቶች ጌታ አንድ ብቻ እንደሆነ እናያለን። እግዚአብሔር አንድ ብቻ ከሆነ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምንድን ናቸው? ወደሚለው ጥያቄ ስንመጣ፤ ሰው አንድ ሆኖ እያለ መንፈስ ነፍስና ሥጋ ያለው እንደሆነ ሁሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ በሶስት መንገድ መገለጹን የሚያሳይ ኢንጂ በአካልም ሆነ በመለኮት ወይም በስም እግዚአብሔር ሶስት መሆኑን አያመለክትም። ስለዚህም ቀጥሎ የተገለጡትን የአብ፤ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ምንነት በዝርዝር የሚያሳዩ የጥቅስ ማስረጃዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስዎ ጋር በማስተያየት በማስተዋል ይመልከቱ።
እግዚአብሔር አብ ብቻዉን ያለና የሚኖር ፍጥረታትን ሁሉ ብቻዉን የፈጠረ የፍጥረታት ሁሉ አምላክና አባት ነው`። ሚል.2፡10 ''ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን?'' 1ኛቆሮ.8፡6 ''ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን ኤፌ.4፡6_7 ''ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሰራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ`።'' እግዚአብሔር አብ መንፈስ የሆነ ሰማይንና ምድርን የሞላ ይህንን ይመስላል ተብሎ የአካል አምሳያ የመይሰጠው የማይሞትና ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን የሚኖር ማንም ሰው ያላየው ሊያየዉም የማይቻለው አምላክ ነው`። /ዮሐ.4፡24`። ኤር.23፡23_24`። ዘዳ.4፡12_19`። 1ኛጢሞ.6፡14_16`። ዮሐ.1፡18 /`።
ዮሐ.1፡1_3 ''በመጀመሪያው ቃል ነበረ...ሁሉ በእርሱ ሆነ...'' መዝ.33፡6 ''...በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ...'' ዕብ.1፡3 ''ዓለሞች በእግዚአብሐር ቃል ኢንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በኢምነት ኢናስተዉላለን`።'' ቆላ.1፡15_17 ''...ኢርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው...በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና...'' 1ኛዮሐ.1፡1 ''...ስለሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረዉን የሰማነዉን በአይኖቻችንም ያየነዉንና የተመለከትነዉን እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን'' ከአብ ዉስጥ መዉጣቱንም ሲያመለክት፦ በዮሐ.16፡28 ''ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ ደግሞ ዓለምን እተዋለሁ ወደ አብም እሔዳለሁ`።ብሏል`።/ዮሐ.13፡3፤17፡8/ ይህ የአብ ቃል በዘመኑ ፍጻሜ የሰዉን ልጆች ለማዳን በዮሐ 1፤14 እንደተጻፈው ''ቃልም ሥጋ ሆነ''`። ዕብ.10፡5 ''...መስዋዒትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ' ይላል`። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና የአብ ቃል በማሪያም ማህጸን አድሮ በመንፈስ ቅዱስ አሰራር ምድራዊ ዘር ያልተቀላቀለበት ሰማያዊ ሥጋ ሆኖ ታየ፤ ተገለጠ`። /1ኛቆሮ.15፡42_57/ የእግዚአብሔር ቃል ሥጋ ሆኖ ተወልዷልና የእግዚአብሔር ልጅ ሆነ`። 1ኛ ዮሐ.1፡1 ''ስለ ሕይወት ቃል... እናወራለን ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን' እግዚአብሔር አብ በሰማይ ብቻዉን ቀርቶ ቃሉን ልኮ ሥጋ በማድረግ ተለያዩን? የሚለዉን ጥያቄ ደግሞ በመቀጠል እንመልሳለን`። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ባዘጋጀው ሥጋ እንደተገለጠ ያስተምረናል`። 1ኛጢሞ.3፡16 ''...እግዚአብሔርን የመምሰል ሚስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው በሥጋ የተገለጠ...'' ማቴ1፡23 ''...እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል...ትርጓሜዉም እግዚአብሔር ከኛ ጋር'' የሚል ነው`። ዮሐ2፡19_21 ''ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሶስት ቀንም አነሳዋለሁ አላቸው...እርሱ ግን ስለ ሰዉነቱ ቤተመቅደስ ይል ነበር`።'' ይህ ቃል እግዚአብሔር አብ የክርስቶስን ሰዉነት የዘላለም ማደሪያአ /መቅደሱ/ አድርጎ ሥጋዉን /አንድያ ልጁን/ በመስቀል ላይ ለሰው ልጆች ቤዛ አድርጎ በመስጠት በሦስተኛው ቀን እንደሚያስነሳውና የራሱ የአብ ሰዉነት ሆኖ እንደሚኖር ያሳያል`። ቆላ2፡9 ''በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰዉነት ተገልጦ ይኖራልና'' ይላል`። 2ኛ ቆሮ.5፡19 ''..እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና `።'' ማለቱ እግዘብሔር አብ ራሱ ወደ ምድር ወርዶ በክርስቶስ ማለትም ባዘጋጀው ሥጋ /በወልድ/ ዉስጥ ሆኖ የሰዎችን ልጆች ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር`። ቆላ1፡20_23 ''እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር በእርሱም በኩል በመስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና... በሥጋው ሰዉነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ'' ይላል`። ስለዚህም በዮሐ.14፡8_9''ጌታ ሆይ አብን አሳየንና ይበቃናል'`። ለሚለው የፊልጶስ ጥያቄ ''ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታዉቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል እንዴትስ አንተ አብን አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?'' ብሎ በመመለስ አብ በሥጋው ዉስጥ የተገለጠ ራሱ የሱስ መሆኑንና መንፈስና ሥጋዉን ነጣጥሎ ማሳየት እንደማይቻል የማይለያይና የማይነጣጠል የአንዱ አምላክ የሥጋና የመለኮትነት ብህርይ መሆኑን ኣስረድቷል። ኢሳይያስም በትንቢቱ ''ህጻን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል'' /ኢሳ.9፡6/ ብሎታልና ህጻኑ /ወልድ/ የዘላለም አባት /አብ/ ከሆነ ከኢየሱስ ዉጭ አብ አለ ብሎ ማመን ከእግዚአብሔር ጋር አያጣላምን? በመዝ.2፡2_3 ''አህዛብ ለምን ያጉረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገስታት ተነሱ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሁ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ ማሰሪያቸዉን እንበጥስ...''ኣሉ ይላል። ዳዊት ይህን የትንቢት ቃል ከተናገረ ከብዙ ዘመናት በኍላ የሃይማኖት ሊቃዉንት ነን የሚሉ ተነስተው ኣብን ወልድን መንፈስ ቅዱስን በመከፋፈል ለአብ አንድ አካል ለወልድም ሌላ አካል ለመንፈስ ቅዱስም ከሁለቱ የተለየ ሌላ አካል አለው በማለት አንዱን አምላክ ብዙ አማልክት አድርገው ለማሳየት በመሞከር ብዙ ክርክርና ዉዝግቦች ተካሄደዋል። ቆላ.2፡8_9 '' እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ ፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ። በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰዉነት ተገልጦ ይኖራል።'' ብሎ ሐዋሪያው ጳዉሎስ ወደ ወደ ሰዎች ፍልስፍና እንዳንዞር አስጠንቅቋል። ስለዚህ የእግዚአብሔር አብ ሙላት በወልድ ዉስጥ መገለጡን ማወቅ ይኖርብናል ማለት ነው። ስለዚህ በ1ኛዮሐ.2፡23 እንደተጻፈው ''ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለዉም በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው' ይላል።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል ያለው ከእግዚአብሔር የተለየ ሌላ አምላክ ሳይሆን ከአብ
ሊለይ የማይችል የእግዚአብሔር አብ ሕያው እስትንፋስ ነው`። ኢዮብ 33፡4 ''የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ '' ይላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንደ ዘይት፣ ነፋስ፣ዝናብ፣ ዉሃ፣እሳት፣ርግብ መመሰሉ ሥራዉን ለማሳየት እንጂ ዘይት፣ዝናብ፣ዉሃ፣እሳት ወይም ርግብ ነው ማለት አይደለም`። እንግዲህ እግዚአብሔር ''ታዉቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንኩ ታስተዉሉ ዘንድ' ኢሳ.43፡10`። ማለት አዉቃቹ እመኑኝ፣ አዉቃቹ አምልኩኝ ማለቱ ነው`።/ዮሐ.4፡22_24`። ሐዋ.17፡23/ ጌታ ኢየሱስ በዮሐ.8፡31፡32 ላመኑበት አይሁድ ሲናገር ''እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእዉነት ደቀመዛሙርቴ ናችሁ፦ እዉነትንም ታዉቃላቹ እዉነትም አርነት ያወጣችኍል አላቸው'`። ስለዚህ እርስዎም እዉነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት የሆነዉን፣ /1ኛዮሐ.5፡20_21/ ያለዉን የነበረዉንና የሚመጣዉን፣ /ራዕይ 1፡5_8፣ 17፡18/ ንጉሳችንንና ጌታችንን ብቻዉን ያለዉን ኢየሱስ ክርስቶስን /ይሁዳ ቁ.4 / በማወቅና በማመን ከኃጢአትና ከዘላለም ሞት አርነት እንዲወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን`።
|
|
||||||||||||||||||||||||||||||||||
![]() |
![]() |
|||||||||||||||||||||||||||||||||||