|
||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አማላጅ አንድ ብቻ መሆኑን አዉቃችኃል? በአዳም መተላለፍ ምክንያት የሰው ዘር በሙሉ በክርስቶስ ሥጋና ደም መስዋዕትነት ካልሆነ በቀር በሌላ መስዋእት በማይሰረይ የሞት ዕዳ ላይ ወድቋል። ሞትም በክርስቶስ ሞት ካልሆነ በቀር በሌላ አይደመሰስም። ሮሜ.5፡15፥21፣ ዕብ.10፡1_8፣ 1ኛጴጥ.1፡18_21፣ ኢሳ.25፡8። የገሃነም እሳትን ሞት የሚያስከትል መተላለፍ በሄዋን ምክንያት ከተፈጸመ በኃላ እግዚአብሔር ከአንቺ የሚወለደው የእባቡን ራስ ይቀጠቅጣል ያለዉን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ሲል ክርስቶስ ከድንግል ማሪያም ተወለደ። ዘፍ.3፡15፣ ገላ.4፡4። በኢሳይያስም አፍ በቀራኒዮ ተራራ ላይ ሊያደርገዉ ያሰበዉን ቃል ኪዳን ሲያበስር፡ ''የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ ያደርጋል። በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለዉን መጋረጃ በአህዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋዉን መሸፈኛ ያጠፋል። ሞትን ለዘላለም ይዉጣል ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ የህዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል እግዚአብሔር ተናግሮአልና'' በማለት የገሃነም ሞትን በክርስቶስ ሞት እንደዋጠው ያረጋግጥልናል። ኢሳ.25፡6_8። በክርስቶስ ሥጋ መቆረስና በደሙ መፍሰስ ምክንያት ስለሞት ፍርሃት በባርነት ታስረን የነበርን ሁላችን ከዲያብሎስ የማስፈራራት ቀንበር ነጻ አወጣን። ዕብ.2፡14። አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር አማላጅና ተማላጅ ሊሆን እንዴት ይችላል? ይላሉ። እግዚአብሔር በልጁ ሥጋና ደም የዘላለም ሕይወት ዋስትና ቃል ኪዳን እንደገባልን ይረሳሉ። ''ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠታ የዘላለም ሕይወት አለው፣ በመጨረሻም ቀን አስነሳዋለሁ'' የሚለዉን ቅል ኪዳን ወደ ጎን ይጥላሉ። ዮሐ.6፡35_59 ዘላለም ማለት እኮ አሥር፣ ሃያ፣ ወይም ሰማንያ ዓመት ማለት አይደለም፤ ''እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸዉም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ህግ አርነት አዉጥቶኛልና'' የሚለዉንም መለኮታዊ የነጻነት አዋጅ ይዘነጋሉ። ሮሜ.8፡1_2 ''እግዚአብሔር የመረጣቸዉን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔርም ቀኝ ያለው ደግሞም ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው'' በማለት የጸና የአማላጅነት ቃል ኪዳን በክርስቶስ እንዳለን ያረጋግጥልናል። ሮሜ.8፡31_39፣ መዝ.89፡1_3 በማስተዋል ያንብቡ። መጽሐፍ ቅዱስ፦ ''ደም ሳይፈስ ሥርየት የለም'' ስለሚል ከክርስቶስ ደም በስተቀር ሰዉን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቅ የሚችል ሌላ ሕያው አማላጅ የለም። ዕብ.7፡15_28፣ ምዕ 9፡14 ቁ.22 1ኛጴጥ.1፡18_21፣ሐዋ.20፡28። የመዳን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን የሚዘነጉ ሁሉ በቆላስያስ 2፡16 ያለዉን የአዲስ ኪዳን መንገድ ይስታሉ።ኤፌ.2፡1_22 በማስተዋል ያንብቡት። ሐዋርያው ዮሐንስ፦ ''ከእርሱ ጋር ህብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እዉነትም አናደርግም ነገር ግን እርሱ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ህብረት አለን፣ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል፤ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እዉነትም በእኛ ዉስጥ የለም። በኃጢዓታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻዲቅ ነው' ይላል። 1ኛዮሐ.1፡6_10 ''ልጆች ሆይ፣ ኃጢአትን እንዳተደርጉ ይህን እጽፍላችኃለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻዲቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተሰሪያ ነው ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፣ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጥዓት እንጂ'' በማለት የማይረታ ጠበቃና ዋስ ክርስቶስ እንዳለን በማይዋሽ ቃሉ አረጋግጦልናል። 1ኛዮሐ.2፡1_2። እዉነት እዉነት እላችሁዋለሁ፣ ወአደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባና ወንበዴ ነው'' በማለት በሌላ አማላጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት መምጣት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ያረጋግጣል። ዮሐ.10፡1 ብጽዕት ድንግል ማሪያም እንኳን በምድር እያለች በቃና ዘገሊላ ለማማለድ ሞክራ ከኢየሱስ የተሰጣት መልስ፡ ''አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ?'' የሚል ስለነበር ''የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ'' አለቻቸው ይላል። ዮሐ.2፡4_5 ስለዚህ ኢየሱስ ያለንን ብቻ ማድረግ ይገባናል። ኢየሱስ ''እኔ መንገድና እዉነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም'' ብሎ ሌላዉን በር በራሱ ዘግቶታል።ዮሐ.14፡6 ሰው ሁሉ ዋስትና ያለው ጠበቃ እያለለት ለምን በከንቱ ይባክናል? በዮሐ.10፡1_12 ደግሞ፦ በበሩ/በክርስቶስ/ሥጋና ደም በኩል ካልሆነ በቀር በሌላ ፈጽሞ መግባት እንደማይቻልና እርሱን ካልያዙ መዳን እንደሚቀርባቸዉም አረጋግጦ አስጠንቅቆአል። በጎቹ ግን በበሩ በክርስቶስ ሥጋና ደም በኩል የመግባት ዕድል አላቸው። ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ መሆኑን ረስቶአል። ቃሉ፦''አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛ /አማላጅ/ ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ''በማለት ኃጠተናዉን ከመለኮቱ ጋር የሚያስታርቅ የክርስቶስ ሥጋና ደም በመካከላችን እንዳለልን አረጋግጦልናልና፣ ሳናወላዉል በቃሉ ታምነን ልንድንበት ይገባል። አንዳድ ሰዎች መላዕክት ስለሚያማልዱ ልመናና ስግደት ሊቀርብላቸው ይገባል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ፦ እያንዳንዱ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣ ያለምንም ልመና መልአክ በአጠገቡ እንዳለዉና ከክፉ ነገር ወይም ከሰይጣን እንደሚታደገው ይናገራል። ማቴ.18፡10፣ መዝ.34፡7። 19፡1_16 ዘካ.3፡1_10። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ምዕመኑ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ አንድ አምላክን ብቻ የሚያመልክ ስግደትም ለአንድ አምላክ ብቻ መሆኑን የሚያምን የሆነ እንደሆን ብቻ ነው።ኢሳ.42፡8፣ ዘካ.3፡1_8፣ መዝ.34፡6፥10፣ሐዋ.5፡17_21፣ምዕ12፡6፥11 መላእክት ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያዉቃሉና፣ መላእክት እንዲሰገድላቸው አይፈቅዱም።ራእይ.19፡9_10፣ምዕ22፡8_9። መላዕክት የንሰሃ ልብ የሌለዉን ኃጢአተኛ አይወዱም። እግዚአብሔር ኃጢአተኛዉን ሊቀስፉ ሲልካቸዉም አይምሩም።2ኛነገ.19፡35_37፣ ሐዋ.12፡23። መላእክት፦ እና እዉነተኞች የእግዚአብሔር አገልጋዮች ስንሆን ከኢግዚአብሔር ተልከውልን የሚረዱን ከአደጋም የሚጋርዱን ረዳቶ ቻችን ናቸው። መዝ.91፣ ዕብ1፡14። ከመለኮት ጋር የማስታረቅ ቃል ግን በወንጌል በኩል በክርስቶስ ብቻ መሆኑ ስለተጻፈ በወንጌል ስብከት አምነው በክርስቶስ ደም ለሚታመኑ ብቻ በሩ ክፍት ነው። ሮሜ.1፡16. 1ኛቆሮ1፡18_25። አንዳንድ ሰዎችም፦ የሞቱት ጻድቃን በእንቅልፍና በእረፍት ላይ እንዳሉ ዘንግተው በምድር በቅዱስ ቃሉ ሥርአት በሐይወት በነበሩ ጊዜ ሲሰሩት የነበረዉን የተአምራት ተግባር ከሞት በሁዋላም ለማከናወን የሚችሉ አስመስለው ይናገራሉ። ከሞት በሁዋላ ተአምራር እንዳያከናዉኑ ሞት አንደከለከላቸው፣ተንተዉም እንዳሉና የመስማትም ኃይል እንደሌላቸው ግልጽ ነው። ገነትና ሲአኦል በአንድ አካባቢ በነበሩበት ጊዜ እንኳን አይችሉም ነበር። መዝ(88)፡10፣ ሉቃ.16፡19_31፣ ዕብ.7፡20_28 የትንሳኤ በኩር ክርስቶስ ብቻ እንጂ ሌሎች ቅዱሳን በሙሉ በገነት አንቀላፍተው ነው ያሉት። አይሰሙም በትንሳኤ ቀን ብቻ ይነሳሉ፤ በቀኝም ይቆማሉ። በፍርድ ቀን ዋስ ጠበቃ አቁሞ መከራከር የለም። ማቴ.25፡31_46 ክርስቶስ ሲፈርድ በአንድ ቃል ግራና ቀኝ ተለያይተው ወደየተመደበላቸው ቦታ መሄድ ብቻ ይሆናል። የገሃነም ልጆች ወደ ዘላለም ስቃይ፣ ጻድቃኖች ደግሞ ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ። 1ኛተሰ.4፡13_18፣ 1ኛቆሮ.6፡2፣ ገላ.5፡16 ክርስቲያን ሆይ! የክርስቶስን ሥጋና ደም አትናቅ። ዕብ.10፡19_31። የእግዚአብሔር ቃል፦ ''የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ፣ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ደም የቆጠረ የጸጋዉንም ደም ያክፋፋ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችሁዋል? ይላልና። ለዘላለም የተገባልህን የመዳን መንገድ ጥለህ ሊሰሙ ሊያዩም ወደማይችሉ ራሳቸዉንም ሊያድኑ ወደማይችሉ ወደ ሰዎችና ወደሌሎችም አማልክት እንዳትዞርና እንዳይፈረድብህ ተጠንቀቅ። እግዚአብሔር ቀንተና አምላክ ነዉና ጥቅሶችን በማስተዋል አንብበህ ተረዳ። ዘጸ.22፡20፣ ሮሜ.1፡20_25፣ መዝ.(46)፡3_4፣ ኤር.17፡5_8፣ ራእይ.19፡9፥10። 22፡8፥9፣ምሳሌ.16፡25፣18፡10፣ ማቴ.11፡27_30፣ ዮሐ.11፡25_27፣ሐዋ.4፡12፡፤ ለዘላለም በገሃነም ከመሰቃየት ለመዳን ዋስትና ያለዉን አማላጅ ኢየሱስ ክርስቶስን አጥብቀህ ብትይዝ ይሻልሃል!! ነገ ሞት እንድይቀድምህ የመዳን ቀን አሁን ነው ይላልና አሁኑኑ ከኢየሱስ ጋር ለመስማማት ፍጠን። 2ቆሮ.6፡2፣ ሮሜ.8፡1_2 ከሞት በሁዋላ ንስኃ የለም። ''የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያዉቁ የራሳቸዉንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፣ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም'' ይላልና፤ የራስህ ጽድቅ የእዉነት ጽድቅ መስሎህ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አትጣል። ሮሜ.10፡1_3" " አይሁዶች የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያዉቁ የራሳቸዉን ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ በፍርድ ላይ እንደወደቁና በዘላለም ሞት እንደተቀጡ ልትረሳው አይገባም። እንግዲህ አስብ! ከዘላለምም ሞት ለመዳን በእግዚአብሔር መንገድ ላይ ተራመድ። የመዳን ቀን አሁን ነው!
|
|
||||||||||||||||||||||||||||||||||
![]() |
![]() |
|||||||||||||||||||||||||||||||||||