|
ልትድን ትወዳለህን?
ታውቀዉና ትፈጽመው ዘንድ የሚገባህ እንደሚከተለው ነው፣
" መዳን በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና"፣
ሐዋ.4፡12
ከመንፈስ ጭንቀት፣ ከርኩሳን መናፍስት መውጊያዎች፣ከደዌ ሁሉና ከዘላለም ሞት ማለትም ከገሃነም እሳት ለመዳን ትፈልጋለህን?
እነሆ የዓለምን ኃጢአትና ስቃይ፣ በሽታም ለመደምሰስ መንፈስን ሰላምና የዘላለምን ሕይወትን እንዲያው ለመስጠት የመጣው የእግዚአብሔር
በግ ኢየስይስ ክርስቶስ እጆቹን ዘርግቶ "ኢናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣እኔም አሳርፋችኍለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔም የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ ቀንበሬም
ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነዉና።" እያለ ወደ እቅፉ ይጠራሃል። ማቴ.11፡28_30፣
ዮሐ.4፡24፣
ክርስቶስ ክፉ ከሆነው ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደሞተ፣እንደተቀበረና ኢንደተነሳ ብታምን ከተጨነክበት የሞት መንገድ
አሁን ሊያወጣህ የተዘጋጀ የዓለም ብርሃን ነው።
እዉነትን ብታውቅ እዉነት አርነት ያወጣሃል። "እዉነት ምንድነው? ትል ይሆናል።
እዉነት ክርስቶስ ነው። እዉነት የሆነው ክርስቶስ እኔና አንተን የሞት መርገም ከተሸከመው ፈራሽ ሰዉነት ፍጹም ወደሆነው ወደ
ሁለተኛው አዳም ማለት ወደ ክርስቶስ በዳግም ልደት አሰራር ይለዉጠን ዘንድ በማይበሰብስና በማይፈርስ( በሕያው) ሥጋ ተገለጠ።
የሞትና የሲኦል ምክፈቻ በእጁ ነው። ራእይ.1፡17_18
ከመጀመሪያው አዳም የወረስነው ይህ ደካማው አሮጌው ሥጋ የሰማይን መንግስት ሊወርስ እንደማይችል ስለሚያውቅ እግዚአብሔር ሰማያዊ
አዳም ሆኖ በሥጋ ተገለጠ። እናንተ ደካሞች ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ከድካማችሁ አሳርፋችኃለሁ፣ ከሥጋዊ ሕይወት ወደ መንፈሳዊ
ሕይወት አሻግራችኃለሁ አለን። ማቴ.11፡28፡፤ 1ኛቆሮ.15፡45_50።
እነሆ የመለወጥ ቀን አሁን ነው። ዳግም የመወለድም ቀን አሁን ነው። ከአንድ ቀን በኃላ ወይም ከአንድ ሰዓት በኃላ አይደለም።
ከድካምህ ከሚያስጨንቅህም ከዚህ ከማይረካው ከአዳማዊ ሕይወት ሰላም ወደምትገኝበት ወደ ሁለተኛው አዳም ወድ ክርስቶስ ተለወጥና
ክርስቶስን በመምሰል በሕይወት ኑር።
"ክርስቶስን መምሰል እንዴት እችላለሁ?" ትል ይሆናል።
"ሰው ከዉሃና ከመንፈስ ካልተወለድ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም"
የሚለዉን መለኮታዊ አዋጅ እንመርምር። ዮሐ.3፡5፣ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፣
ይህም ማለት ከአዳም ዘር የተወለደ አዳማዊ ነው፣ አፈር ነዉና ወደ አፈር ይመለሳል ማለት ነው። ሥጋና ደም ደግሞ የእግዚአብሔርን
መንግስት ሊወርሱ አይችሉም፣ የሚበሰብሰዉም የማይበሰብሰዉን አይወርስም ተብሎ ተጽፏል። 1ኛቆሮ.15፡50።
ክርስቶስ ግን ሰዉም መንፈስም ነው። 2ኛቆሮ.3፡17 ሰዉነቱም የማይበሰብስ፣
መቃብርን ድል ነስቶ በዘላለም ሕይወት የተነሳ የአምላክ ሥጋ ነው።
ስለዚህ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን ምሰሉ፣ ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ ግን መንፈስ ነው ያለው። አንተም
ክርስቶስን ለመምሰል ከውኃና ከመንፈስ መወለድ አለብህ። ዮሐ3፡5_7።
'የክርስቶስን ሥጋ እንዴት እለብሳለሁ?" ትል ይሆናል።
መጽሐፍ ቅዱስ፦ 'ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ ኢያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፣ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።" ይላል።
ሐዋ.2፡38_39።
በስሙ በመጠመቅ ከእርሱ ከክርስቶስ እንደምንወለድ ከዚህ በላይ የተጻፈው ጥቅስ ያመለክታል። በኢየሱስ ስም የተጠመቁት ሁሉ
ክርስቶስን እንደለበሱ ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦ "እናንተ ሁላችሁ የእግዘብሔር ልጆች ናችሁና ከክርስቶስ ጋር አንድ
ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኃልና"። ገላ.3፡26_27።
ደግሞም ቲቶ.3፡5 "አንደምህረቱ መጠን፣
ሀ/ ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና
ለ/ በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን እንጂ፣
እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም ይላል።
ባጭሩ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች ለመረዳት የምንችለው አዲስ ልደትን ለማግኘት ከአዳም ዘር እንዴት እንደምትለይና በአዲሱ
አዳም ማለት በክርስቶስ ሥጋ ዉስጥ ለዘላለም እንዴት እንደምትኖር ነው።
በኢየሱስ ሥም በጠመጠመቅ አዲሱን አዳም "ክርስቶስን" ስለ ለበሱት ሰዎች ጳዉሎስ ሲጽፍ፦ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ
ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ነገር (አዳማዊ ሥጋ) አልፎአል እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል"። 2ኛቆሮ.5፡17።
አንተም ንስሃ ገብተህ ለኃጢአትህ ስርየት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመጠመቅ ካልተቀበልከው በቀር አሁን በለበስከው የአዳም
ሥጋ ሆነህ የነፍስ እረፍትንና ኢርካታን ለማግኘት ፈጽሞ አትችልም። የመንፈስ እረፍት ያስፈልግሃል። የሚያውክህና የሚያስጨንቅህ
ሌላ አይደለም። ይህ አሁን በላይህ ላይ ያለው ምድራዊ አዳም ምንም ብታስጌጠውና ብትንከባከብለት ፈጽሞ የማይረካና በቃኝ የማይል
ባዕድ ጠላትህ (ማለት የነፍስህ ጠላት) በመሆኑ ከሰይጣን ጋር በመተባበር ነፍስህን ስለሚያዉክ ሰላምን ለማግኘት አያስችልህም።
ገላ.5፡17_24 1ኛቆሮ.6፡9_11።
ከለበስከው ጠፊ አካል ለመዳን አሁን ብትወስን ክርስቶስን (ሕይወትን) ለብሰህ በሰላም መኖር ትችላለህ።
በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አለብህ፤
ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብ ክርስቶስን ከለበስክ የዘላለም ርስት መያዣ የሆነውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል ያስፈልግሃል።
ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን የሚለዉን አስተዉለህ አንብበው። ቲቶ.3፡5።
ከአሮጌው አዳም ወጥተህ ክርስቶስን የምትለብሰው ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብ ማለት በስሙ በመጠመቅ ነው። ሐዋ.26፡17።
1ኛቆሮ6፤9_11።ማር.16፡16። ሐዋ.19፡1_6።
በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ማለት ምን ማለት ነው?
አዳም ሲፈጠር በመንፈስ ነበር የተፈጠረው። ኢዮብ.32፡8 34፡4። ዘፍ.2፡7
ተመልከት። ነገር ግን አዳም የእግዚአብሔርን መንፈስ ስላረከሰ እግዚአብሔር እንደገና መንፈሱን በመስጠት የአዳምን ነፍስ ለማደስ
ፈቀደ።
አንተም የማይሞት ነፍስና የሚሞት አካል (ሥጋ) ያለህ ሰው ስለሆንክ የሚሞተው ሥጋ ተችሮ ወደማይሞት የክርስቶስ ሥጋ ስትለወጥ
ነፍስህ ደግሞ በእግዚአብሔር መንፈስ መታደስ ይኖርበታል። ስለሆነም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አስፈላጊነቱ ለነፍስህ መታደስ
ነው ማለት ነው። በመንፈስ ቅዱስ ካልታደስህ በቀር ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት አትችልም።
መንፈሱን እንዴት አገኛለሁ? ትል ይሆናል።
እግዚአብሔር መንፈሱን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ያለ አድልዎ እንደሚሰጥ በኢዩኤል.2፡28።ሐዋ.2፡1_4
በዮሐ.7፡37_39። ለመመልከት ትችላለህ። ቃሉ እንዲህ ይላል፦"በአለ ሃምሳ የተባለዉም ቀን (የጴንጤቆስጤ
ቀን) በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓዉሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትንም
ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፣ በያንዳንዳቸዉም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፣
መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው ይናገሩ ጀመር። ይላል። መንፈስ ቅዱስ በመሞላት በሌላ ልሳን መናገር ለአንተም ጭምር
የተፈቀደ ነው። ሐዋ.2፡17_21፣ ማር.16፡17፣
በማቴዎስ 3፡11 እንደተገለጸው በመንፈስ ቅዱስ አጥማቂው ኢየሱስ ስለሆነ ፊትን አይቶ የማያዳላ
የልብ አምላክ ነዉና ለቀደሙት ሁሉ እንደሰጠ ኢንደ ሰጋው ብዛት መንፈሱን ያፈስልሃል። ስለዚህ መንፈሱን ለመቀበል በመጠማት
ልብህን ከፍተህ በጌታ ፊት ተንበርክከህ ብትጸልይ በመንፈስ ቅዱስ ትሞላለህ። ሕይወትህም ይታደሳል።
ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለድህ ግን ወደ እግዚኣብሄር መንግስት ልትገባ አትችልም፡፡ ዮሃ
3፡5
ኢየሱስና አብ አንድ ናቸው
የተለያየ እምነት ያላቸው ሰዎች ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ኢየሱስ ፍጡር ሆኖ ተራ ነብይ ነው ይላሉ።
ኢየሱስ ራሱን ለደቀመዛምርቱ ሲያስተዋውቅ ማን ነኝ አለ?
ፊሊጶስ አብ ለብቻው በሰማይ የቀረ ሌላ አምላክ መስሎት አብን አሳየንና ይበቃናል ብሎ (ኢየሱስን) በጠየቀ ጊዜ፦ ኢየሱስም
(አብም) "አንተ ፊሊጶስ፣ ይህን ያህል ዘመን(33 ዓመት) ከእናንተ ጋር ስኖር አታዉቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፣
እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳይን ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?" ብሎታል። ዮሐ.14፡8_10
"በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው፤እኔና አብ አንድ ነን" የሚሉት ቃል በማስተዋል ብትመለከተው ኢየሱስ
ራሱ ኢብ እንደሆነ ለመገንዘብ ትችላለህ።ዮሐ.10፡30፣ 1ኛዮሐ.2፡23።
"በመጀመሪያ ቃል ነበረ፦ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፦ ቃል ሥጋ ሆነ" ይለናል። ዮሐ.1፡1_14፣
ፊተናይቱ ትእዛዝ እስራኤል ሆይ ስማ አምላክህ እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፣ እርሱንም በፍጹም ልብህ ዉደድ የምትል
እንደሆነች ተጽፎኧ። ዘዳ.6፡4፣ ማር.12፡29
አምላካችን በአብነት ከዘላለም እንደ አባት የተገለጠ፣ ሚል.2፡10፣
በወልድነት ደግሞ ህዝቡን ለማዳን ሥጋን ለብሶ በሰዉነት እንደተገለጠ፣ ማቴ.1፡20_23፣
በመንፈስ ቅዱስነት ደግሞ ሕዝቡን ለማደስና ለመቀደስ በሦስት መንገድ መገለጹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመገንዘብ እንችላለን።
ሐዋ.2.1_4፣ 2ኛቆሮ.3፡17።
በምጽአት ጊዜ በምድር ሊነግስ ሲገለጽም "እግዚአብሔር አንድ ስሙም አንድ ይሆናል" ይላል።
ዘካ.14፡9"
ጳዉሎስም "ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሰራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ" ይላል።
በሮሜ 9፡5 "ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉም በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው አሜን"
ይላል።
በቆላስይስ 2፡9 ደግሞ "በእርሱ(በክርስቶስ) የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰዉነት ተገልጦ ይኖራል"
ይላል። እግዚአብሔር በሥጋ ተገለጠ፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። 1ኛጴጥ.3፡18፣
1ኛጢሞ.2፡5፣ ኢሳ.7፡14፣ 9፡6፣
በ1ኛ ጢሞ.3፡17 "በእዉነትም ታላቅ ነው የአምልኮት ምስጢር፦ አምላክ
በሥጋ ተገለጠ
በመንፈስ ጸደቀ
ለመላዕክት ታየ
በአህዛብ ተሰበከ
በዓለም ታመነ
በክብር አረገ" ይላል።
እግዚአብሔር አንድ ነው እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። 1ኛጢሞ.2፡5፣ ጌታህም
አምላክህም ኢየሱስ ነዉና በእርሱ አምላክነትና ሰው መሆን ብታምን ይበቃሃል። መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ
የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና"" ሐዋ.4፡12፣
|