default homepage contact shop forum articles amharic bible frendship doctrin home

If you are not read this Amharic tract just get from hear NOW by cliking this

home page
doctrin
singls
amharic bible
article
public forum
sale
contact
tell a frend
 

ጥምቀት ያድናል !!


1ኛ ጴጥሮስ 3.20 22
የሐዋ ሥራ 22፥16
       "ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚኣብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" ። ተብሎ ተጽፎአል። ዮሐ፣ 3፥5።
       የዘመኑ ስመ ክርስትያኖችእምነት እንጂ ጥምቀት አያድንም ይላሉ ።ምን አምነው እንደሚድኑ ግን አላስተዋሉም ።ጥምቀት ያድናል ብለው ቢያምኑ ኖሮ ጥምቀቱ የሚከናወነው በመድሃኒቱ በኢየሱስ ስም ስለሆነ ሊያድናቸው ይችል ነበር ።
       ምን አምነው እንደሚድኑ አላስተዋሉም ሲባል በኢየሱስ አምነን ነዋ !ይሉ ይሆናል። ኢየሱስ ግን ከውሃና ከመንፈስ ያልተውለደ ሰው ወደ መንግስቴ አይገባም ብሎ ደንግጎአል ።
      ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ /ሐዋርያት/ እንዃን በጥምቀት እንደዳኑ ሲመሰክሩ፤
    "ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን"ብለዋል።ቲቶ 3፥5
    ሃናንያም ጳውሎስን ፥"ኣሁንስ ለምን ትዘገያልህ ?ስሙን እየጠራህ ተጠምቅ ከኃጢአትህም ታጠብ"በማለት ለደህንነቱ እንዲጠምቅ አጣደፈው።ያልተጠመቀ ሊድን አይችልምና።
   በኖህ ዘመን የነበሩት ሰዎች ባለመታዘዝ ጠንቅ ሲጠፉ ቃሉን የታዘዙት 8 ነፍሳት ግን በውሃ ምክንያት ወደመርከብ ገብተው (ተጠምቀው) አንደዳኑ ተጽፎአል። 1ኛ ጴጥሮስ 3፣19_22።
    እስራኤላውያንም ከፈሮንና ከሰራዊቱ ሁሉ እጅ (ከሞት) ሊድኑ የቻሉት በውሃ እንደሆነና ያም ውሃ የጥምቀት ምሳሌ እንደነበረ ተጽፎአል  ዘጽ14 1ኛ ቆሮ 10፥1_3
ጥምቀት በእርግጥ ያድናል፤ነገር ግን የማያምኑበትን ሊያድን ስለማይችል ያመነ የተጠመቀም ይድንበታል ካላመነበት ግን ሊያድነው አይችልምና ኣምኖ ኣለመጠመቁ ያስኮንነዋል ማር16 16       መጠመቅ ማለት ከክርስቶስ ጋር በስሙ አማካኝነት መቀበርና ክርስቶስን ልብሶ በአዲስ ህይወት መነሳት ማለት ነው ሮሜ 6፤3_5
     በኢየሱስ ስም መጠመቅ ያነጻል፣ ይቀድሳል ያጸድቃል።1ቆሮ 6፥11።መጽሃፍ፥ "ንስሐ ግቡ፤ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በእየሱስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ" ይላል። የሃዋሥራ 2፣38።
  ብዙ ሰዎች፥ጥምቀት ዋጋ ያለው ነገር ስለማይመስላቸው ባንጠመቅም ለመዳን እንችላለን እያሉ ለፍርድ ራሳቸውን አዘጋጅተዋል። ጥምቀት ጽድቅን ለመፈጸም ብቻ ይጠቅማል ብለው በዮሃንስ ጥምቀት ተጠምቀው የነበሩትም ለኃጢኣታቸው ስርየት ኣስፈላጊ እንደሂነ አምነው ዳግመኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደተጠመቁ ተጽፎኣል ሐዋ19፥1_6 ሐዋ ሥራ፥43_48።
     ኢየሱስ ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ አንደሰጠ እኛም በንስሃ ራሳችንን ለእየሱስ መስጠት አለብን። እርሱ እንደሞተና እንደተቀበረም ለኣለምና ለርኩሰት ሞተን ከእርሱ ጋር በጥምቀት መቀበር ኣለብን። ከሙታን በድል ለዘላለም በሕይወት እንደተነሳም በጥምቀት ከተቀበርንበት ክርስቶስን ለብሰን በአዲስ ህይወት ለዘላለም መነሳት አለብን ።ነገር ግን ጥምቀት ያለ እምነት እምነትም ያለ ጥምቀት ሊያድን አይችልም። በእምነት ያልሆነ ሁሉ ሐጢኣት ነውናሮሜ14፥23 ሮሜ6፥3_5።
     ጥምቀት ሊከናወን የሚገባው በኢየሱስ ስም ብቻ ነው ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በባህር እንደተጠመቁ እኛም ክርስቶስን ለመተባበር በስሙ መጠመቅ ስለሚገባን ነው፡ 1ኛቆሮ10፥1_3
      ደግሞም የኃጢአታችንን ሥርየት የምናገኘው ኢየሱስ በተባለው ስም ብቻ ስለሆነ ነው ማቴ1፥21 ሉቃስ24፥17 የሓዋ ሥራ 4፥12፡የሐዋ ሥራ 10፥43_48። ማንኛውም መለኮታዊ ተግባር በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ እንድናደርግ ከመለኮት ስለታዘዝን ነው፡
     ታዲያ ከኢየሱስ ጋር ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ያለ ጥምቀት ለምን ዳነ? የሚሉ ብዙ ናቸው ወንበዴው የዳነው የኤዲስ ኪዳን ጥምቀት ማለትም ከኢየሱስ ጎን የፈሰሰው ውሃና ደም በስሙ  ለሃጢኣት ሥርየት መጠመቅ ከመጀመሩ በፊት በነበረው የንስሃ የመንጻት ሥርዓት በፊት ነው።ጌታ ኢየሱስ፣"ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" "ኃጢአትሽ ተሰረየችልሽ" እያለ ከሃጢኣት ሲፈታቸው  የነበርው ከመሞቱ በፊት ነበር፡።ሞቶ ከተነሳ በኃላ ግን ሰው ከውሃና ከመንፈስ እንዲወለድ በደነገገው ስርዓት እንጂ በቀደመው የመንጻት ሥርዓት መዳን አልተቻለም።ስለዚህ ነው ብዙዎቹ የዮሃንስ ደቀመዛሙርት እንደገና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጠመቁት። የሓዋሥራ19፥1_6።
የመዳንን መክፈቻዎች ለሃዋርያት ያስረከበው ከበዓለ ሃምሳ ቀን ጀምሮ ስለሆነ ሐዋርያት በሰሙት የመዳን መክፈቻ ቃላት መሰረት ማለት፥በእየሱስ በማመን፣ ንስሃ በመግባት፣ በኢየሱስ ስም ለሃጢኣት ስርየት በመጠመቅና በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ያልዳኑ ሁሉ ወደእግዚኣብሄር መንግስት ሊገቡ እንደማይችሉ ቃሉ በግልጽ ይመሰክራል ገላ1፥8_12 /1ኛ ዮሃንስ 4፣6 ሉቃስ 10፥10 ማቴ16፥18_15 ይሁዳ ቁ 3_4ቁ 17_25 ዮሃ  3፥5፡።ቲቶ 3፥5
መዳን የሚገኘው ለቃለመለኮት በመታዘዝ ነውና ንሰሃ ገብቶ ለሃጢአቱ ስርይት ያልተጠምቀ ሊድን አይችልም። ቃሉን የሚፈጽመው እንጂ አቤት ባዮች ሁሉ ኣይድኑም ማቴ7፥21_23 ሉቃ 7፥30 ሉቃ11፥28





.

.

.

የዕለት እንጀራዬ
አርብ
ህዳር 12 ቀን
1ሳሙኤል
ምዕራፍ 4-6

( November = 21
ሮሜ
ምዕራፍ 1-5)

.