|
||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
የማንን እንስማ? የስውን ወይስ ክርስቶስ ኢየሱስ ያለዉን እንስማ? መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እንጂ የሰው ቃል እንዳይደለ አረጋግጦ ማመን እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህን በመጀመሪያ እወቁ በመጽሐፍ ያለዉን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደለትም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ ፪ኛ ጴጥ1፡20፡21። ኢሳ34፡16። ሰው የሚለው፦ የኢየሱስን ወይስ የጴጥሮስን እንስማ በማለት መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለት አካፍሎ የሰዉና የእግዚአብሔር አድርጎታል። ኢየሱስ የሚለው ግን የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስትያኔን እሰራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር የምታስረው በሰማያት የታሰረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል የሚል ነው። ማቴ 16፡17_19። ሐዋ 2፡38። ሰው የሚለው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር የኢየሱስና የመንፈስ ቅዱስ የማዳን ስም ነውና ለጥምቀት ስንጠቀምበት ያድነናል የሚል ነው። ኢየሱስ የሚለው ግን፦ የእግዚአብሔር አብም የወልድም የመንፈስ ቅዱስም አዳኝ ስም ኢየሱስ የተባለው ስሜ ብቻ ስለሆነ ለእግዚአብሔር አብ ክብር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ አድርጉት ነው፣ ማቴ.1፡20_23፣ ሉቃ.24፡47፣ ቆላ.3፡17፣ ፊሊ.2፡9_11፣ ሐዋ.4፡12፣ ዮሐ.5፡43፣ 16፡23_24፣ 17_26፣ ሰው የሚለው፦ አብና ወልድ በሰማይና በምድር ለየብቻቸው በየአካላቸው ይኖሩ ስለነበር ወልድ ወደሰማይ እያየ ይጸልያል ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ እኔና አብ አንድ ነን እኔ በአብ አብም በእኔ ዉስጥ በተዋሕዶ እንዳለን እመኑ እመኑ እመኑ ነው፣ ዮሐ.10፡30፣ ዮሐ.14፡6_10፣ ኢየሱስ ኢርግጠኛዉን የሚያስተምር የማይዋሽ መምህርና ስለራሱም ከራሱ በላይ የሚያዉቅ ሌላ ስለሌለ እዉነት ኢዉነት እልሃለሁ የምናዉቀዉን እንናገራለን ያየነዉንም እንመሰክራለን ምስክራችንንም አትቀበሉትም ስለምድራዊ ነገር በነገርኃችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማያት የሚኖረው የሰው ልጅ ነው በማለት ራሱ እንደ አብ በሰማይ ሙላት እንደ ወልድ በምድር መኖር የሚችል እንደነበር አረጋግጦአልና የአብና የወልድን የአካል አንድነት ከወልድ ስለተማርን የአካል አንድነቱን ልንክድ አንችልም፣ ዮሐ.3፡11_13 ሰው የሚለው፦ የአንድነታቸዉን ገመድ እንበጥስ ነው ንጉስ ዳዊት ሲመሰክር አህዛብ ለምን ያጉረመርማሉ?ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገስታት ተነሱ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሁ ላይ እንዲ ሲሉ ተማከሩ ማሰሪያቸዉን እንበጥስ ገመዳቸዉንም ከእኛ እንጣል፣ በሰማይ የሚኖር ኢርሱ ይስቃል ጌታም ይሳለቅባቸዋል፣ በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል፣ በመአቱም ያዉካቸዋል ይላልና፣ (መዝ.2፡1_5) ኢየሱስ የሚለው፦ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይህም በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ሁሉም በእርሱ ሆነ ከሆነዉም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም ቃልም ሥጋ ሆነ "እኔን ያየ አብን አይቷል" "እኔና አብ አንድ ነን ይላል" ዮሐ.14፡7_11፣ ዮሐ.1፡1_14፣ 10_30፣ ሰው የሚለው፦ የኢየሱስ ሥም አጋንንትን ለማስወጣትና ፈውስ ስንፈልግ የምንጠራው እንጂ ለኃጢአት ስርየት ስንጠመቅ አንፈልገዉም ነው፣ ኢየሱስ የሚለው ግን፦ ሐዋሪያትን የሚሰማ እኔን ይሰማል እነርሱን የጣለ እኔን ይጥላል እኔንም የጣልለ የላከኝን ይጥላል ይላል፣ ሉቃ.10፡16 ፣ ለእናንተ የመንግስተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኃል ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም ማቴ.13፡11 ስለዚህ ሐዋሪያት ምስጢሩ ስለገባቸው በእየሱስ ሥም ብቻ ሲያጠምቁ ኖረዋል ሐዋ.2፡38፣ ሐዋ.8፡16፣ ሐዋ.10፡43_48፣ 22፡16፣ የማይለወጥ የዕምነት አንቀጻቸዉንም በኤፌሶን ቤተክርስቲያን ሲደነግጉ" በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት (በኢየሱስ ስም ብቻ የሆነች) ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሰራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ ብሎአል፣ ኤፌ.4፡4_6፣ ሐዋ.19፡1_6፣ ሰው የሚለው፦ አንድ አምላክ በአንድ አካል በኢየሱስ ተገልጦአል የሚሉአብንና መንፈስ ቅዱስን ክደዋል ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው ነው፣ 1ኛዮሐ.2፡23፣ ዮሐ.3፡13፣ ዮሐ.14፡6_10 ሰው የሚለው፦ መንፈስ ቅዱስ እንደሰው አካል የሆነ አካል አለው ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ስለሆነ እንደ ነፋስ አንደ ደመና እንደ ዘይት የሚመስል እንጂ ሥጋና አጥንት እንዳለው በሰው አካል አይመሰልም ነው፣ ኢዮብ.32፡8፣ 33፡4፣ ዘፍ.2፡7፣ ሐዋ.2፡1_4፣ ዮሐ.20፡22፣ ሰው የሚለው፦ በዘፍጥረት 1፡26 እንፍጠር ስለሚል በሰማይ ሦስት ፈጣሪዎች ነበሩ ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ በዘፍጥረት 1፡26_27 እግዚአብሔርም "አለ" በማለት በነጠላ ቁጥር አንድነቱን ያመለክታል፣ ቁጥር 27 ደግሞ ሰዉን "በመልኩ ፈጠረ" በእግዚአብሐርም መልክ "ፈጠረው" በማለት በነጠላ ቁጥር አንድነቱን አረጋግጦ በማሳየቱ አንድ እንጂ ሦስት ሆኖ አያውቅም፣ በኢሳ.44፡6_8 ቁጥር 24 ደግሞ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኃለኛ ነኝ ከእኔ ሌላ አምላክ የለም እንደ እኔ ያለ ማነው? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም፣ ከማህጸን የሰራህ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ሁሉን የፈጠርሁ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ? እያለ ይጠይቃል፣ ሰው የሚለው፦በዳግም ምጸት ጊዜ አብና መንፈስ ቅዱስ በሰማይ ቀርተው ወልድ ብቻውን ይመለሳል ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ አምላኬ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል...እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሳል በዚያን ቀን እግዚአብሔር አንድ ስሙም አንድ ይሆናል (ዘካ.14፡1_9 ተመልከት) ሰው የሚለው፦ የአብ ልጅ እግዚአብሐር ወልድና የማሪያም ልጅ ክርስቶስ በተዋህዶ አንድ አካል ናቸው የሚል ሲሆን፣ ኢየሱስ የሚለው፦ እኔና አብ በተዋህዶ አንድ አካል ነን የሚል ነው ዮሐ.1፡1_14፣ ዮሐ.14፡6_10አንድ ወልድ የአብ ልጅ እንጂ ሁለት ወልዶች የሉምና፣ ክ325 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1050 ዓ.ም ድረስ የነበሩትን ክርክሮች ከቤተክርስቲያን ታሪክ ተመልከት፣ ሰው የሚለው፦ ሚካኤል ወልድ ለመሆን ከድንግል ማሪያም ተወለድ እንጂ ቃል ሥጋ አልሆነም ነው(የጆሆቫ ምስክሮችን ጠይቅ) ኢየሱስ የሚለው፦ ዕብ.1፡5_6 "ከመላዕክትስ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጅሃለሁ ደግሞም እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞስ በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይሰግዳሉ ይላል "እኔና አብ አንድ ነን በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል" ነው ዮሐ.12፡44_45፣ ዮሐ.14፡7_11፣ ሰው የሚለው፦ በሐዋ.2፡38 ያለው የኢየሱስ ስምጥምቀት ለአይሁድ ብቻ ነው አይሁድ አብንና መንፈስን ስለሚያውቁ ኢየሱስን ግን ስላልተቀበሉት ወልድን ለማስተዋወቅ የተደረገ ጥምቀት ነው የሚል ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ የሰው ነፍስ ሁሉ በኢግዚአብሔር ፊት ስለረከሰ ያለ ኢየሱስ ስምና ደም መታረቂያ መዳኛ የለዉምና ነፍስ ሁሉ እንዲድን ከሰማይ በታች ከኢየሱስ ስም በቀር መዳና የለዉም ነው፣ ሉቃ.24፡47፣ ዮሐ.14፡6_7፣ ሐዋ.2፡38፣ ሐዋ.4፡12፣ ሮሜ.5፣ ዮሐ.1፡12፣ 3፡16_18፣ በአይሁድና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለም ተብሎ ተጽፏል፣ ሮሜ.2፡11፣ 3፡20_26፣ ሮሜ.10፡12_13፣ ገላ.3፡26_28 ሰው የሚለው፦ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ብቻ ተጠቅልሎ አንድ አካል አንድ ፈጣሪ ሆነ ስሙም ኢየሱስ ብቻ ነው የሚሉ አብንና መንፈስን ክደዋል ነው፣ ኢየሱስ በቃሉ የሚለው ግን፦ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፣ ...ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስ ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለዉም በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት፣ማንም ወደናንተ ቢመጣ ይህንንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት በማለት ያወግዛል 2ኛዮሐ.7_9 የክርስቶስ ትምህርት ምንድነው? ብለን ብንጠይቅ በዮሐ.10፡30 እኔና አብ አንድ ነን ይላል በዮሐ.14፡6_11 አብና ወልድ በተዋህዶ፣ መንፈስ በሥጋ፣ ሥጋ በመንፈስ ዉስጥ በአንድ አካል እንዳሉ ያስተምራል ክርስቶስ እኔን ያየ አብን አይቶአል ብሎ ያስተምራል ሐዋሪያትም የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰዉነት (በሥጋ) ተገልጦ ይኖራል ይላሉ፣ አምላክ በሥጋ ተገለጠም ይላሉ፣ አማኑኤል ሆነም ይላል ማቴ.1፡23፣ ኢሳ.7፡13_14፣ ቆላ.2፡8_9፣ 1ኛጢሞ.3፡16፣ ይሁዳ ቁጥር 4 "ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፣ ንጉሳችንንና ጌታችንንም ብቻዉን ያለዉን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ... ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ በክብሩ ፊት በደስታ ነዉር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው ብቻዉን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን... ኃይልም ስልጣንም ይሁን አሜን" ይላል ቁ.24_25፣ ስለ ስሙም ሲናገር እኔ በአባቴ ስም መጣሁ በማለት ኢየሱስ አብ በሥጋ ሲገለጥ የተጠራበት ስም እንደሆነ ይገልጣል፣ ዮሐ.5፡43፣ ሚኪ.5፡2_4፣ ኤር.23፡5_6፣ ዕብ.1፡3_4፣ ራዕይ.3፡12፣ ማቴ.1፡20_23፣ ሰው የሚለው፦ እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ እግዘብሔር መንፈስ ቅዱስ በየአካላቸው አሉ ነው፣ ኢየሱስ በቃሉ የሚለው ደግሞ፦ አንድ እግዚአብሐር አብና ሰው የሆነው ክርስቶስ ብቻ እንጂ ሶስት እግዚአብሔሮች የሉም ነው የእግዚአብሔር ልጅ በማለት ፋንታ እግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር እስትንፋስ የሚል አልተጻፈምና፣ 1ኛጢሞ.1፡15_17 1ኛጢሞ.2፡5_7 1ኛጢሞ.3፡16፣ ዮሐ.17፡3 1ኛዮሐ.5፡19_20፣ ሰው የሚለው፦ ኢየስሱስ የዳዊት ዘር የሴት ዘር የተባለለት እንደ እኛ ሰው ስለሆነ ዘመን የሚቆጠርለት ነው የሚል ሲሆን ኢየሱስ የሚለው፦ ያለዉና የነበረው የሚመጣዉም ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል...እንዲህም አለኝ አትፍራ ፊተናውና መችጨረሻው ሕያዉም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ(ሞትን ለዘላለም ለመዋጥ ኢሳ.25፡8) እነሆም ከዘላለም (ዘመን ከማይቆጠርለት) እስከዘላለም ድረስ ህያው ነኝ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ በማለት የሞትን ከንቱነት ለማሳየትና ሞትንም ለዘላለም ለመዋጥ ኢንጂ ዘላለማዊ ሕያዉነቱ እንዳልተነካ ያረጋግጣል፣ ራዕይ.1፡8 ቁ.17_18፣ ሚክ.5፡24 1ኛዮሐ.1፡3፣ ዮኀ.1፡1_14፣ ኤር.23፡5_6፣ ርዕይ.5፡13 ሰው የሚለው፦ መላዕክት ስግደት ሊቀበሉ ይገባል የሞቱ ጻድቃንም ሆኑ ሕያዋን መላዕክት በእነሱ ስም ብንጸልይ ያማልዳሉ ነው፣ ኢየሱስና መላዕክት የሚሉት ግን፦ "ሰዎች ያለ መሐላ ካህናት ሆነዋልና ክርስቶስ ግን፦ ጌታ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን እንዳልሆነ መጠን እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ሆኖአል እነርሱም እንድይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል"፣ለእነርሱም አማላጅ ስለሚያስፈልጋቸው ሊያማልዱ አይበቁም ዕብ.7፡20_28 መላዕክትም እግዚአብሔር ቀናተኛና ክብሩን ለማንም የማያካፍል መሆኑን አዉቀውና ፈርተው ለኢኛ እንዳትሰግዱ ተጠንቀቁ ብለው በራዕይ.19፡9_10፣ 22፡6_9፣ ኢሳ.42፡8፣ አስረድተዋል፣ ሰው የሚለው፦ 318 ሊቃውንት በንቂያ የወሰኑት ቃለ ጉባኤም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ይታመንበታልና መመሪያችን ነው የሚል ሲሆን ኢየሱስ የሚለው፦ በቃሌ ላይ የሚጨምር ወይም ነጥብ እንኳ የሚቀንስ መቅሰፍት ይጨመርበታል ነው፣ ማቴ.5፡16_20፣ ገላ.1፡6_12፣ ራዕይ.22፡18_20፣ ማር.8፡38፣ 2ኛቆሮ.11፡1_4፣ 2ኛጴጥ.3፡16_18፣ ሰው የሚለው፦ በእግዚአብሔር ግራና ቀኝ የተቀመጡ እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሉ የሚል ሲሆን፣ ኢየሱስ የሚለው፦ "እነሆም ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ በማለት በሰማይ አንድ ዙፋንና አንድ ተቀማጭ ብቻ እንዳለ ነው ራእ.4፡2 "በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉ ይሁን" በማለት በአንዱ ዙፋን ላይ የተቀመጠው አብ የተዋሐደው ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ ያረጋግጣል በአንድ ዙፋን ሦስት ነገስታት አይቀመጡምና፣ ከእርሱ በፊት አምላክ የለም ከእርሱ በኃላም አይሆንም፣ ኢሳ.43፡10_12፣ 44፡6_8፣ 44፡24፣ ሰው የሚለው፦ የተወለደዉም የሞተዉም እግዘብሔር ነው የሚል ሲሆን ኢየሱስ በቃሉ የሚለው ግን፦ ወላጅ አባቱ አብ የተወለደው ሰው የሆነው ክርስቶስ የእግዚአብሔ ልጅ እንደሆነ ነው 1ኛጢሞ.2፡5_7፣ "በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና አጥንት የለዉምና እኔን ዳሳችሁ እዩ" ብሎአቸዋልና ሉቃ.24፡39፣ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የማይታመን ከእግዚአብሔር አይደለም ተብሎም ተጽፏልና 1ኛዮሐ.4፡1_3፣ 2ኛዮሐ.ቁጥር 7፣ስለዚህ ኢየሱስ በሥጋ ሲሞት በመንፈስ ግን የዘላለም አባት ነዉና ሕያው ነው 1ኛጴጥ.3፡18፣ ኢሳ.9፤6 ራእይ.1፡8 ቁ 17_18፣ ሰው የሚለው ግን፦ የአንድ አምላክ አማኞች ሦስት ስላሴን ይክዳሉ ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦ ብቻዉን ያለዉን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ ነው ይሁዳ.3_4፣ ኢሳ.44፡6_8 ቁ 24 ዘጸ.20፡3_5 ሰው የሚለው፦ በሥላሴዎች ስም መጸለይ ይገባናል ነው፣ ኢየሱስ የሚለው፦"እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ" ነው ዮሐ.16፡24፣ በሰማያት ያለው አባት አንድ ብቻ ስለሆነ አባቶቻችን ሆይ ሳይሆን አባታችን ሆይ በሉ ይላል፣ ስሞቻችሁ ይቀደሱ ሳይሆን ስምህ ይቀደስ በማለት ነጠላ ቁጥርን ያመለክታል በጸሎትም ጊዜ አንድነቱን እንድናዉጅ ያዛል፣ ማቴ.6፡9_10፣ ዘዳ.6፡4፣ ኤፌ.4፡6 ሚል.2፡10 "ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?" ኢሳ.9፡6፣ ሰው የሚለው፦ በዘፍጥረት 18 የተጠቀሱት ሶስት ሰዎች ስላሴዎች ናቸው ነው፣ የኢየሱስ ቃል ግን፦ ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸዉን አቀኑ ወደ ሰዶምም ሄዱ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር፣ በማለት መላዕክት እንጂ እግዚአብሔሮች እንዳልነበሩ ያረጋግጣል፣ ዘፍ.18፡22፣ 19፡1_4 ቁትር 13፣ አልሸሹም ዘወር አሉ እንደሚባለው ዶክተር እሼቱ አባተና የመለሰ ወጉ የተምታታ ሃሳብ ያዘሉ የስድብ መጻህፍት የአንድ አምላክ ትምህርት ለተገለጠላቸው ለእኛ ድጋፍ ሆነው በመገኘታቸው በገዛ ልሳናቸው መረታታቸዉን ያመለክታል፣ መጽሐፍ ቅዱስ መናፍቅ የሚለው ብቻዉን ያለዉን አንዱን አምላክ ሦስትም ዘጠኝም የሚሉትን ነው በእግዚአብሔር ቃል የተወገዘው የነቱርተሊያንን ፍልስፍና አንግቦ ከመወናበድ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ማመን ይሻላል፣ ቆላ.2፡8_10 እግዘብሔር አብ በሥጋ ተገለጠ ስሙም አንድ አካሉም አንድ መለኮትነቱም አንድ ብቻ ነው፣ የአንድ ሰው ቃልና እስትንፋሱ የአካል ሦስትነት እንደማያሰጡት እንዲሁ አብም መለኮትነቱ ቃሉና (ሥጋው) እስትንፋሱ ሦስት አካላት አያሰጡትም፤ አንድ ነው፣ ለእዉነተኛ ዳኝነት መጻሕፍቶቻቸዉንና መጻሕፍቶቻችንን አንብቡና እውነቱን ያዙ ዉሸቱን ጣሉ፣ |
|
||||||||||||||||||||||||||||||||||
![]() |
![]() |
|||||||||||||||||||||||||||||||||||