default homepage contact shop forum articles amharic bible frendship doctrin home

If you are not read this Amharic tract just get from hear NOW by cliking this

home page
doctrin
singls
amharic bible
article
public forum
sale
contact
tell a frend
 

መርምረኝ አትጣለኝ

ኢየሱስ ባስተማራቸውና የሰማይን ምስጢራት ሁሉ በገለጠላቸው ሐዋርያት መሰረት እምነት የምትከተከተል ሃዋርያዊት ቤተክርስቲያን የምታምነው እንደሚከተለው ነው::

ከመስቀል ዉሃና ደም በዘላለም መንፈስ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ስንጠመቅ ተገኙ::ሶስቱም ለማዳን በአንድ ይስማማሉ::
1ኛ-ዮሐ 5:6-8, ቁ.19:20, ሉቃስ 24:47, ዮሐ 4:12, ቲቶ 3:5-7, ዮሐ 10:43።

1ኛ ጥያቄ፡- የክርስቲያን መሰረት ማነው?

መልስ ፡- ክርስቶስ ራሱ ነው። ክርስቶስ ራሱም የመሰረታት ሃይማኖት አንዲት ቅድስት የሐዋሪያት ቤተ ክርስቲያን ናት።
ኤፌ 2-20, ሐዋ 2:38-42, ማተ 16:18-19, 1ኛ ቆሮ 3:1-11

2ኛ ጥያቄ፡- ጴንጤቆስጤ ማለት ምን ማለት ነው?በመጽሐፍ ውስጥ ይገኛል?

መልስ በግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስና በአሮጌው አማሪኛ መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ "በጴንጠቆስጤ ቀን" እያለ በሐዋ 2፡1 ተጠቅሶአል። ትርጓሜዉም መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን ቀን የሚገልጽ የመንፈስ ቅዱስ በዓል ወይም የነጻነት በዓል ማለት ነው። ዘሌ 23:4-16, ዘጸ 12:, 1ቆሮ 16:8

3ኛ ጥያቄ፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ የሚሆንበት አንደምን ነው?

መልሱ ፡ አብ መንፈስ ነው። መንፈስም አንድ ነው። የማይወሰን ጽንፍ የሌለው በሁሉ የሚገኝ ስፋቱ ረዝመቱ ይህ ነው የማይባል ነገር ግን በስጋ ሊገለጥ ሲፈልግ በመንፈሱ አሰራር በድንግል ማሪያም ማህጸን ቃሉን ስጋ አድርጎ በልጁ ዉህደት ራሱን ለአለም የገለጸ በመሆኑ አንድ አምላክ ነው።
የዳዊት መዝ(139):7-11, ማቴ 1:20-23, 1ኛጢሞ 2:5-3,16, 2ኛቆሮ 5:19, ዮሐ 1:1-14, ቆላስይስ 2:9, ዕብ 1:3, ኢሳ 9:6,

4ኛ ጥያቄ፦ መንፈስ ቅዱስ ከማን ይወጣል? ወይም ከማን ይሰርጻል? አካሉስ ምን አይነት ነው?

መልስ፦ ከአብ ወይም ከኢየሱስ የሚወጣ መለኮታዊ ሃይል ወይም የእግዚአብሄርነቱ እስትንፋስ ነው። ኢዮብ 3:3_4, ሮሜ 8:9, ዘፍ 2:7, ዮሐ.20:22, መንፈስ ቅዱስ የሐዋ 2፡17 ከአብ ወይም ከኢየሱስ ውስጥ የሚወጣ መለኮታዊ ኃይል አንጂ ከግራ ወይም ከቀኝ ተነስቶ የሚላላክ ሌላ ኣምልክ አይደለም። ቲቶ 3:6-7, ኢዮ 2:38, የሐዋ 2:1-17,
አስትንፋስ በመስፈሪያ ስለማይለካ በቁመትም በወርድም ስለምይለካ እፍ አያለ የሚሰጠው የማይመጠን በየጊዜው ከአግዚአብሔር የሚፈስ የመለኮት አስትንፋስ ነው።

5ኛ ጥያቄ፦ የአብና የወልድ ልዩነት ምንድነው?

መልስ፦ አብ መንፈስ ነው። ዮሐ 4፡23-24 አግዚአብሔር በስጋ ተገለጠና ሰውና መንፈስ ሆነ። ኢሳ 2፡6 ሰው ስለሆነ ልጅ ሆነ። ፍጹም አምላክ በመሆኑ የዘላለም አባት ነው። ስለዚህ አብና ወልድ አንድ ነው። ዮሐ 14:8-10, 1ኛጢሞ 2:5, 1ኛ ጢሞ 3:16, ዮሐ 1:1-14, 2ኛ ቆሮ 5:19, ቆላ 2:9, 1ኛ ጴጥ 3:18, ዮሐ 14:6, ዮሐ 2:19-22, ማቴ 1:20-23,

6ኛ ጥያቄ ወልድ ያለው አብ አለውን?

መልስ፥ ወልድ ያለው አብ አለው ።ወልድ የሌለው ግን አብ አንኳን የለዉም። ምክንያቱም አግዚአብሔር በስጋ ተገልጦአልና ።
ዕብ.5:7-10, 2ኛ.ቆሮ 5:19, ቆላ.2:8-9, 1ኛዮሐ.2:2-24, ዮሐ.14:7-11, ኢሳ.7:14, ኢሳ.9:6, ዮሐ.8:18-19, ዮሐ.10:30, 1ኛጢሞ.1:15-17, 2:5:7, ሉቃ.10:22, ማቴ.11:27-29, ዕብ.10:5-7,

7ኛ ጥያቄ፦ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ትክዳለህን?

መልስ፦ አልክድም በትክክል አብ ወልድ አና መንፈስ ቅዱስ አንድ አካል አንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ በመገንዘብ አምናለሁ። ኢየሱስ የሚል ስም የመለኮት ስም አንደሆነና መለኮት በስጋ ሲገለጽ እንደተጠራበትም አምናለሁ። መንፈስ ቅዱስ የአብ እስትንፋስ እንደሆነ አንጂ ከአብ ዉጪ አካል አንደሌለው አምናለሁ።
ዮሐ.4:24, የሐዋ.5:3-4, ኢዮብ.32:8, 33:4, ዮሐ.5:43, ዮሐ.17:3-6, ማቴ.1:20-21, ፊሊጵ.2:9, ዮሐ.1:1-14, ኢሳ.9:7, ሚል.2:10,

8ኛ ጥያቄ፦ ሐዋርያት ለምን በአብ በወልድ አና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ታዘው በኢየሱስ ስም አጠመቁ?

መልስ፦ ወልድ ያለው አብ አለው። ወልድ የሌለው ግን አብ እንኳን የለውም ስለሚልና መዳንም የአብና የወልድ ሥም በሆነው በኢየሱስ ብቻ እንደሆነ መልአኩ ገብርኤል ስለመሰከረና ክርስቶስም ኢየሱስ በተባለው የአብ ስም እንደመጣ ስለመሰከረ በአዳኙ በኢየሱስ ስም አጠመቁ።
የሐዋ.2:38, የሐዋ.4:12, የሐዋ.10:33፣48, ሉቃ.24:47, ማቴ.1:21, ፊሊ.2:9, 1ኛዮሐ.2:12, ቆላ.3:17, ሚኪ.5:2-4, ኤር 23:5-6, አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ የማዕረግ ስም እንጂ የተጸወኦ ስም ስላልሆነ አላጠመቁበትም። በማዕረግ ስሞች ማጥመቅ አልተማሩምና።

9ኛ ጥያቄ፦ ጥምቀት እንዴት ኃጢትን ያስተሰረያል?

መልስ፦ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚጠመቀው በፍጹም ጸጸትና ንስሃ ወደ ኢየሱስ ተመልሶ በእምነት ሲጥመቅ ከክርስቶስ የወጣው ውኃና ደም በስሙ አማካኝነት ኃጢአትን ሲለሚደመስስ ጥምቀት የመዳን ጸጋ ያስገኛል።
የሐዋ.2:38;10:48, ሉቃ.24:47። ዮሐ.3:5, ቆላ.2፡11-14, 1ኛዮሐ.5፡6-8, የሐዋ.22:16, ገላ.3፡27, አማኝ ሲጠመቅ በደሉና ሞት የተፈረደበት አዳማዊ ስጋው ተገፎ በምትኩ ክርስቶስን በእምነት ለብሶ በአዲስ ሕይወት እንዲኖር ያበቃዋል።

10ኛ ጥያቄ፦ የተጠመቀ ሰው ዳግም ሊጠመቅ ይችላልን?

መልስ፦ ከሐዋሪያት ስርዓተ ጥምቀት ዉጪ የሆነ ጥምቀት የተጠመቀ ሰው ካለ ጥምቀቱ ከንቱና የዉኃ ዋና ይሆንበታል። በኃጢያቱም እንደታሰረ አለ። ማቴ.16፡18-19። ወይም እንደመጥምቁ ዮሐንስ ትምቀት ይሆንበታልና የኤፌሶን ክርስትያኖች ዳግም እንደተጠመቁ ሊጠመቅ ይገባዋል። ኃጢአቱን ተናዞ ለኃጢያቱ ሥርየትናክርስቶስን ለመልበስ በኢየሱስ ስም በጥልቅ ውኃ ከተጠመቀ ግን መልካም አደረገ። ኤፌ.4:5, የሐዋ.19:1-6, ማር.16፡16, ያመነ የተጠመቀም ይድናል ያላመነ ግን ስለማይጠመቅ ይፈረድበታል። ማንኛዉም ሰው ክርስቶስን የሚለብሰው በስሙ ሲጠመቅ ብቻ ነው። ገላ.3፡27, ገላ.1፡8-9, ቆላ.2፡11-14, ከክርስቶስ ጋር በጥምቀት ካልተቀበረና አሮጌዉን አዳም ኣስገፍፎ አዲሱን አዳም ክርስቶስን ካልለበሰ እራቁቱን ነው።
ሮሜ.6:3-8, ቆላ.2፡11-14, ገላ.3፡26-27, 1ኛቆሮ.15፡39-50, ሮሜ.8፡1-3, ቁ29-30, ራእይ.16፡15, ማቴ.22፡11-14,

11ኛ ጥያቄ፦ ያለ ኢየሱስ ስም ጥምቀትና ያለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሰው ሊድን ይችላል? ዳግምስ ሊወለድ ይችላል?

መልስ፦ሊድን አይችልም። ሰው ከዉኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር መንግስተ ሰማያት ለመዉረስ ፍጹም አይችልም ሲል ኢየሱስ አስረግጦ አዉጇል።
ዮሐ.3፡5, ኤፌ.1፡13-14, 1ኛቆሮ.12፡13, ማቴ.3፡11, ሉቃ.11፡13,

12ኛ ጥያቄ፦ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለድ የማይድን ከሆነ ከጌታ ጋር የተሰቀለው ወንበዴ ያለ ጥምቀት ለምን ዳነ?

መልስ፦ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሯ በፊት ከ አዳም ጀምሮ እስከ ትንሳኤው ድረስ የነበሩት ሰዎች በሕግና በተስፋ እንደዳኑ እንጂ በዳግም ልደት ጥምቀት ኢንዳልዳኑ መጻህፍት ይመሰክራሉ። 1ኛጴጥ.3፡18-19, ቁ4፡6, ከጌታ ትንሳኤ በኃላ ከ ጴንጤቆስጤ ቀን ጀምሮ ግን ከጌታ ጋር መቀበርና መነሳትን ለማረጋገጥ በጥልቅ ውኃ በኢየሱስ ስም ለኃጢያት ስርየትተጠምቀው በኪዳኑ ደም ታጥበው በመንፈስ ቅዱስ የታተሙ የተቀደሱ ምእመናን ይሆናሉ ነው። ከዚያ በፊት ግን ክርስቲያን የሚባል የለም። ከጴንጠኾስጤ ቀን ጀምሮ በሃዋርያት ትምህርት የተፈታ ይሆናል እንጂ ከስቅለትና ከትንሳኤ በፊት እንደነበረ ስራት ቢሄድ ሊድን አይችልም። በሃዋርያት ትምህርት ያልተፈታ ግን በሰማያት የታሰረ ይሆናል
ማቴ.16:18-19, የሐዋ.2:38, ገላትያ 1:8-9, ገላትያ 3:27, ዕብ.19-20, የሐዋ.22-16,

13ኛ ጥያቄ በዘፍ 1፣26 እግዚአብሄር እንፍጠር ማለት ሥስት ፈጣሪዎች ኣሉ ማልቱ ነው?

መልስበዘፍ 1:26-27 እግዚኣብሄርም አለ ብሎ ይጀምራል ቀጥሎ እንፍጠር ይልና በነጠላ ቁጥር "በመልኩ"በማልት አንድ አካል አንድ አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል "እንፍጠር"ማልቱ ደግሞ እግዚአብሄር ከገዛ ፈቃዱ ጋር እየተማክረ ይፈጥር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በኤፌ.1፡11 እና በኢሳ.44፡24 ያረጋግጣል። እግዚአብሄርን የሚያማክር ሌላ አማካሪ ወይም ረዳት እንዳልነበረው ራሱ አረጋግጦአልና። ዘፍ.1፡26-27። ሁሉን ነገር ብቻውን ለመፍጠሩ ከዚህ በታች ያሉትን ማስረጃዎች በማስተዋል ተመልከት።
ኢሳ.40፡12-15, ኢሳ.40፡28, 1ኛሳሙ.2፡3, ሚል.2፡10, ኢዮብ.33፡4, ኢሳ.44፡8, ይሁዳ.1፡4-5, ዮሐ.1፡1,ቁ27, ዮሐ.2፡7 እግዚአብሔር በአካልም በመለኮትም አንድ ብቻ ነው። ዘዳ.6፡4, ዘዳ.32፡29-41, ዮሐ.3፡13, ዮሐ.17፡3, ዮሐ.5፡20,

14ኛ ጥያቄ እግዚኣብሔር መንፈስ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ከሆነ ሁለት መንፈሶች አሉ ማለት ነው?

መልስ፦ መጽሐፍ ቅዱስ "መንፈስም አንድ ነው።" ስለሚል እግዚአብሔር መንፈስ ነው። የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእዉነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በእውነትና በመንፈስ ሆነን ለአንዱ መንፈስ መስገድ እንዳለብን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ አንድ አካል አንድ መንፈስ አለ ይላል። የእግዚአብሔር መንፈስ ማለት የእግዘብሔርን ሕይወት የእግዚአብሔርም መልኮታዊ እስትንፋስ የሚገልጥ እንጂ ከእርሱ ልዩ የሆነ መንፈስ አለ ማለት አይደለም።1ኛቆሮ.12:3-4, ዮሐ.4:24, በኤፌ.4:4-6,

15ኛ ጥያቄ፦ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በቅርጽ ወይም በስዕል ሶስት ሰዎች አስመስለው የቀረጽዋቸው በሰማይ እንደዚያው በሦስት አካል ይኖራሉ ብለው ስለሚያምኑነው?

መልስ፦ የሥላሴ አማኞች በአገላለጽና በእምነት ይለያያሉ። አንዳንዶቹ ዘጠን መለኮትም እስከማለት የሚደርሱ አሉ። ቤንሂን የተባለው የታወቀ የካርዝማቲክ ሰባኪ ይህን ያመለክታል። አንዳንዶቹም በሶስት አካላትና በሶስት መለኮት በመነጣጠል የሚያምኑ ስለሆኑ የትሪቴይስቲክ ባህርይ ስላለባቸው ሶስት ሰዎች መሳይ እግዚአብሔሮች አሉ ብለው ስለሚያምኑም ሦስት ሰዎችን አስመስለው በመሳል ስዕላቸውን ያስተዋውቃሉ ይሰግዱላቸዉማል። ሌሎቹ የስላሴ አማኞች ደግሞ አንድ አምላክ ይሉና ነገር ግን አብ አምላክ ወልድ አምላክ መንፈስ ቅዱስም አምላክ በአካል ሦስት በስም ሦስት በግብር ሦስት በመለኮት አንድ በማለት ለሰው ግራ የሚያጋባ የመለኮትና የአካል አንድነትና ሦስትነት ይገልጻሉ። ምን ማለታቸሁ ነው ?ተብለው ሲጠየቁ ምስጢር ነው ዝም ብለህ እመን ይሉናል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እግዚአብሔር በአካልም ሆነ በመለኮት ግራ በማያጋባ ሁኔታ አንድነቱን ይገልጻል።
ሮሜ.1:20-25, ዮሐ.1:1-14, 1ኛጢሞ.3:16, ይሁዳ ቁ.3-4,ቁ.25, ኢሳ.9፡6, ኢሳ.44፡6-8, ራዕይ.4.2 የኦክስፎርድ ዲክሽነሪ ኦፍክርስቲያን ቸርች "የስላሴ አማኞች በአሳባቸው እዉነተኛ በአገላለጻቸው ግን የሦስት አማልክ አማኞች ናቸው"ሲል ያጋልጣቸዋል´። ገጽ 1396 2nd edition F.L.Cross.

16ኛ ጥያቄ፦ የሥላሴ አማኞች ሥላሴን በዕንቁላል ይመስሉታ። እንቁላል ሦስት አካል አላት ወይ?

መልስ፦እንቁላል አንድ እንጂ ሦስት አካል የላትም። እግዚአብሔርም ሦስት መስሎ ይታያቸው እንጂ እስትንፋሱን ቃሉንና ልቡን አወላልቀው በሦስት ቢከፍሉት ሙሉ አምላክ ሊሆንላቸው አይችልም። ይህ በእግዚአብሔር መጫወት ይባላል። ትልቅ ድፍረትም ነው። ኃጢአትም ነው። እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም ይላልና። ሚል.3፡6"አሁንም እኔ ብቻዬን እኜ እንደሆንኩ ከ እኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዪ፤ እኔ እገድላለሁ አድንማለሁ። እኔ እመታለሁ እፈዉስማለሁ ከእጄም የሚያድን የለም" ይላል። ዘዳ.32:39, እግዚአብሔርን እናብዛ ብለው ለሚያስቡ በኢሳ.11:2 መንፈሶች ዘጠኙ ከተቆጠሩና እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ በተጠቀሱት መንፈሴ፣ቃሌ፣ ጽድቄ፣ማዳኔ፣ቸርነቴ፣ፍርዴ ሕጌ ኢሳ.51፡4-17,ኢሳ. 56፡1, መዝ.90:17, መዝ.35፡5-6, ክብሬ ድምጼ ዘፍ.3፡8, እስትንፋሴ፤ ልጄ ነፍሴ፣ ልቤ፣ ደሜ፣ ሥጋዬ፣ እጄ፣ ቀኜ ስለሚል መዝ.89፡13, ኢዮብ.32፡8, ዘፍ.2፣7, እነዚህ ሁሉና ሌሎችም እግዚአብሄር የጠቀሳቸው የባህሪው ክፍሎች በሙሉ በአካል መልክ እየቀረጥጹ መልክ ከሰጡአቸው አማልክትን መፍጠር ይቻላል እንደማለት ይቆጠራልና እንጠንቀቅ። እግዚአብሄር አንድ ብቻ ነው!

17ኛጥያቄ፣ እየሱስ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፣ አብ ቀኝና ግራ የለውም፤ ሁሉ በሁሉ የሚገኝ መንፈስ ነው። በአብ ቀኝ ተቀመጠ ማለት ግን የአብ ኃይልና ሥልጣን ወረሰ ወይም መለኮትን ለበሰ ከስጋ ድካም ተለየ የአብ ቀኝ ወይም ክንድ ሆነ ማለት ነው። የአብ ኃይልና ጥበብ ኢየሱስ እንደሆነ ተጽፎአል። 1ኛቆሮ1፡24, መዝ.98፡1, ኢሳ.51፡5,ኢሳ. 53፡1, ኢሳ.59፡16-17, ሉቃ.22፡69, ማቴ.26፡64, ማቴ.28፡18, ዮሐ.16፡24 ዮሐ.15፡16 መዝ.89፡13, የእግዚአብሔር ኃይል በኢየሱስ ስም ዉስጥ ነው። የእግዚብሔር ኃይል በስጋውና በደሙ ይሰራል። ዮሐ.6፡35-59, ራዕይ.11:15:18, ራዕይ.12፡10-12,

18ኛ ጥያቄ መንግስቱን ለአባቱ አስልፎ ይሰጣል ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ሲል ወልድ ፍጡር ነዉና ፍጡር ለፈጣሪ ይገዛል ማለት ነው? 1ኛቆሮ.15፡20-18, 1ኛቆሮ.12፡10-12,

መልስ፦ ቃል ስጋ ሆነ ይላል። ቃልም እግዚአብሔር ነው። ዮሐ.1:1-14። እግዚአብሔር በሥጋ ተገለጠ ይላል። 1ኛጢሞ.3:16, የመስቀል ቃልኪዳን እስከ ምጸአት ቀን ብቻ ነው። ከዚያ በኃላ ግን ወንጌል ማለት የክርስቶስ መሰቀል አይሰበክም። እግዚአብሔር በስጋ ተገልጦ የሚሰራዉን ሥራ ይፈጽማል። ከዚያ በኃላ እግዚአብሔር አንድ ስሙም አንድ ይሆናል። ዘካ.14-9። እግዚአብሐር በስጋው በኩል ሲሰራው የነበረውን ሥራ ከፈጸመ በኃላ ይህንን ተገንዝቦ ያልተቀበለ በልጁ (በስጋው) መገለጡን ያላመነ በልጁ ስልጣን ይፈረድበታል። ሥጋውም በመለኮት መለኮትም በስጋው እንደሆነ ይኖራል። በመስቀሉ ቃል የዳን ግን ሁላችን በሥጋው (በልጁ) ሲገለጥ የነበረውን የማይታይ መለኮታዊ ምስጢርን ፊት ለፊት እንመለከተዋለን። ለዘላለም ከእርሱ ጋር እርሱን መስለን እንኖራለን።
ራዕይ.1:18, ሮሜ.9:5, ቲቶ.2:13, ዘካ.14:5-9, ቆላስይስ.2:8-10, ዮሐ.6:3, ዮሐ.6:60, 2ኛቆሮ.3፡17, 2ኛቆሮ.5፡16, 1ኛዮሐ.3፡17, 1ኛዮሐ.5፡16, 1ኛዮሐ.3፡1-3, ፊሊ.3:20-21,

19ኛ ጥያቄ፦ አብ በልጁ /በሥጋው/ ዉስጥ የተዋሐደ /የከበረ/ ከሆነ ወልድ ወደማን ይጮህና ይጸልይ ነበር?

መልስ፦ ወልድ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው። ፍጹም ሰው ስለሆነ ከመለኮት ጋር ሊያስታርቀን የምልጃ ጩኽት ይጮሃል፣ያለቅሳል፣ይራባል ይጠማል፣ይደክማል፣ ይጸልያል ስለ ሰዎች ለሁሉም ይማልዳል፤ እግዚአብሔርም በልጁ በክርስቶስ /በሥጋው/ ሆኖ ዓለምን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና ይላል። አብ መንፈስ ነው ሥጋና አጥንት የለዉም። ከዘላለም ዘመን ያዘጋጀልንን መዳን ይሰጠን ዘንድ ሥጋን አዘጋጀ፣ ከሥጋውም ጋር ተዋሐደ። ዕብ.10:6, 2ኛ.ቆሮ.5፡19, ዮሐ.6፡57, ዮሐ.14፡8, ዮሐ.4፡24, ቆላስይስ.2፡9, ኢሳ.9፡6, ማቴ.1፡23, 1ኛጢሞ.1፡15-17, 1ኛጢሞ.3፡16, ሮሜ.9፡5, ዕብ.5፡7-11, ሉቃ.24፡39, በሥጋው ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። 1ኛጴጥ.3፡18, ሰው ስለሆነ ሞተ አምላክ ስለሆነ በገዛ ስልጣኑ ተነሳ። አብ ወልድን ወይም መንፈስ ሥጋውን አስነሳ። የሐዋ.2፡24,

20ኛ ጥያቄበ1ኛተሰ.5፡23 ላይ"መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ስጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ" ማለቱ ስው ሦስት አካላት ኖረዉት ሦስቱም በየግላቸው ለፍርድ ይቀርባሉ ማለቱ ነውን?

መልስ፦ የእግዚአብሔር ቃል ሰው የማይሞትና የሚሞት ተፈጥሮ በአካሉ እንዳለው ያረጋግጣል። ዘፍ.2፡7። ሰው ከጭቃና ከመንፈስ እንደተፈጠረ ያረጋግጥልናል። ኢዮብ.32፡8። በሰው ዉስጥ መንፈስ ማለትም የማይሞት ሕያው ነፍስ እንዳለው ያረጋግጣል። በ2ኛቆሮ.4፡16። ደግሞ "የዉጭው ሰዉነታችን /ሥጋችን/ ቢጠፋ እንኳ የዉስጡ ሰዉነታችን /ነፍሳችን/ ዕለት ዕለት ይታደሳል" በማለት ሰው በአንዱ አካሉ መንፈስ ነፍስና ሥጋ እንዳለው እንደ ሦስት አካላት በሚመስል አነጋገር ቢነገርላቸዉም ሰው ሦስት አካል መሆን እንደማይችል ሦስት ሆነውም በየግላቸው ወደ ፍርድ እንደምይቀርቡ ኢርግጠኞች ነን። ሰው በሥጋ ሲሞት ግን ነፍሱ ማለትም መንፈሱ ወደ ገነት ትሄድና አፈር ግን ፈርሶ /በስብሶ/ ይቀራል። ለፍርድ ሲነሳ ግን በአዲስ መልክ በአካል ሙላት ተነስቶ ለፍርድ እንደሚቀርብ ቃሉ ያረጋግጣል። 1ኛቅሮ.15., የሐዋ.7፡59, ያዕ.2፡26, ማቴ.10፡28, ርዕይ.20፡4, መክ.12፡7,

21ኛ ጥያቄ፦ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥም ለኃጢአታቸው ሥርየት ሳይጠመቁ አጋንንትን የሚያስወጡ ትንቢት የሚናገሩ ታላላቅ ሰባኪዎች አልዳኑም ማለት ነው?

መልስ፦ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጴጥሮስ በሰጠው ሥልጣን መሰረት በሐዋ.2፡38 ጴጥሮስ በተናገረው ቃል ያልተፈቱ በሰማይ የታሰሩ ናቸው። ማቴ.16፡18_19, የሐዋ.2፡38_42። መርምረው፣ ኣትለፈው! ማስትንቀቂያ።
ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራት አላደረግንምን? ይሉኛል፤ በዚያን ጊዜ ኢናንተ አመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ ይላል። በማቴ.7፡22_23, እና በማቴ.16፡18_19, መሰረት ፈዋሾች ፈዋሽነታቸው ለደህንነታቸው ዋስትና ሊሆናቸው አይችልም። ጌታ ኢየሱስ የመፍታትና የማሰር ስልጣን ለጴጥሮስ ስለሰጠው ለጴጥሮስ በተሰጡት ሦስት መክፈቻዎች በሐዋ.ሥራ 2፡38 መሰረት ካልተፈተህ በቀር በሰማይ ቦታ የለህም። ጌታ መጥቶ ግራና ቀኝ በሚከፍልበት ጊዜ እንዳታፍር የጴጥሮስን አዋጅ ተቀበል። 2ኛተሰ.1፡8_10።

22ኛ ጥያቄ፦ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፦ ጸጋ ማለት ከእግዚአብሔር እንዲያው በነፃ ያለ ሥራ፣ ያለ ድካም፣ ያለ ዋጋ የተሰጠ የነፃ ስጦታ ማለት ነው።

23ኛ ጥያቄ፦ በጸጋ የተገኙ ስጦታዎች ምንና ምን ናቸው?

መልስ፦ የመስቀል ስጦታዎች ናቸው
ሀ/. ከአባታችንና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶሰ አካል የወጡ ዉኃውና ደም። ዮሐ.19፡34, ዮሐ6፡50_63, 1ኛዮሐ.5፡6_8, ዕብ.9፡14, ዕብ.19_20, የሐዋ.20፡28,
ለ./ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት። ማቴ.3፡11, ሉቃ.12፡49, ሉቃ.11፡13, ቲቶ.2፡5_7, ኤፌ.1፡13_14, የሐዋ.2፡17_18,
ሐ/ የመለኮት ስም "ኢየሱስ ክርስቶስ" ራሱ ጸጋ ነው። ማቴ.1፡20_23። ኢየሱስ ማለት ፦(ደምና ውኃ መንፈስ ያለበት መድኃኒት) ማለት ነው። 2ኛ ቆሮ.3፡3_17, 1ኛዮሐ.2፡12, 1ኛዮሐ.5፡13, ማቴ.3፡11, ዮሐ.2፡12, እነዚህ ጸጋዎች ለደህንነት በአንድ ይስማማሉ አይለያዩም´።

መ/ ጥምቀት ጸጋ ነው። በጸጋ ድነናል ማለት ኃጢአታችንን እየተናዘዝን (ምሳ.28፡13) ሕይወትን በሚሰጥ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለኃጢአታችን ስርየት ስንተመቅ በዘላለም መንፈስ የፈሰሰው ደሙና ዉኃው በጥምቀት በአንድነት በእምነት ብንወስድ ያድኑናል ማለት ነው።
ከዚያም በመንፈስ ቅዱስ መሞላት አለብን። 1ኛዮሐ.5፡6_8, ዕብ.9፡14,ቁ.19-20, የሐዋ.2፡38, ማቴ.3፡5-11, ጥምቀት ራሱ የደህንነትን ጸጋ የሚያሰጥ ስለሆነ ጸጋ እንጂ ሥራ አይደለም። እምነትና ስራም ከተለያዩ ከንቱ ናቸው። ያዕ.2፡18-26።
አስተዉልና የቀደመችዉን መንገድ ያዝ! ኤር.6፡16-21።
ዛሬ ከነጴጥሮስ ጋር በጌታ ቤት መገኘትንም ምረጥ። በኢየሱስ ክርስቶስ ሥም ለኃጢአትህ ስርየት ተጠምቀህ ጸጋዉን ተቀበል። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታንም ተቀዳጅ´። ለነፍስህም እረፍትን፣ሰላምንና ፍቅርንም ታገኛለህ። በእግሮችህ ለመቆም የምትችለዉና ከጥርጥር ነጻ የምትሆነው ከዚያ በኃላ ነው። ለምን ትዘገያለህ{ የኀዋ.22፡16። እዉነትን ብታውቅ እዉነት አርነት ያወጣሃል። ዮሐ.8፡32 ። ቃሉ መርምረኝ ቸል ብለህ አትለፈኝ ይልሃል"" መርምረህ ተረዳና ከጥፋት ዳን።




.

.

.

የዕለት እንጀራዬ
ቅዳሜ
ሰኔ 26 ቀን
ማቴዎስ
ምዕራፍ 27-28

( July = 4
ምሳሌ
ምዕራፍ 14-17)

.