| ..አምላካችን
እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው ዘዳ
6 4 Tell a Friend make home page |
|
|
በክርስቶስ
ትምህርት 2ኛ ዮሐ.9_11 9 ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስ ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ስራው ይካፈላልና:: የእግዚአብሔር ቃል በክርስቶስ ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ እንደሌለው ይረጋግጣል። እዉነተኛ አምላክ የለለው ሰው በራሱ ሰላም ስለማይኖረው ለሌላዉም ሰላም ሊሰጥ አይችልም። ሰላም የሚለዉም ሰው ከክፉ ስራው ጋር ይካፈላል፡ ይሕም ማለት ነፍስን ከሚጎዳ እምነት ጋር ህብረትን መፍጠር እንደማይገባ ማመልከቱ ነው። በክርስቶስ ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለዉም ከተባለ፦ ክርስቶስ ስለ አብና ዎልድ ምን ብሎ አስተማረ? በማቴ.11፡27 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም" ይላል። በዮሐ.17፡33 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።" በማለት ለህይወታችን ደህንነት ጥቅም የአብና የዎልድን የአንድነት ምስጢር ከክርስቶስ ትምህርት መረዳትና ማወቅ እንዳለብን ያስተምራል። በዮሐ.5፡39_40 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤40 ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።" በማለት የዘላለም ህይወት በክርስቶስ መጠቅለሉን ያመለክታል። በዮሐ.10፡30 "እኔና አብ አንድ ነን "ይላል። በዮሐ.14፡6_7ኢየሱስም። እኔ መንገድና
እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር።
ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው።" ወደራሱ እያመለከተ "አይታችሁትማል" በማለቱ የአብንና
የዎልድን ውህደት ምስጢር መናገሩ እንደሆነ ያልተገለጠላቸው ሐዋሪያት ትያቄ ፈጥሮባቸው ነበርና ፍሊጶስ አብ ከክርስቶስ
ዉጪ እንዳለ መስሎት "ገታ ሆይ አብን አሳየንና ይበቃናል" ብሎ ጠይቋል። "ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ ይህንን
ያህል ዘመን ከናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን{ እኔን ያየ አብን አይቷል እንዴትስ
አንተ አብን አሳየን ትላለህ እኔ በአብ እንዳልሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?እኔ የምናገራችሁን
ቃል ከራሴ አልናገረዉም ነገር ግን በእኔ የሚኖርው አብ እርሱ ስራዉን ይሰራል፡፤" (ዮሐ.14፡8_10)
በማለት በማይነጣጠል ውህደት አብ በክርስቶስ ዉስጥ ክርስቶስም በአብ ዉስጥ፤እንዳሉ ያስተምረናል። ነጣጥሎ ለየብቻ
ማየት ስለማይቻል "እመኑ" በሚለው ኃይለ ቃል ሳያወላውሉ ውህደቱን እንዲቀበሉ አስረግጦ አዟል። በዮሐ.12፡44_45 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም
አለ። በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።" ስላለ በክርስቶስ
ኢየሱስ ብቻ የሚያምን በስጋ የተገለጠዉን አብን ማመኑ ነው እንጂ አብ ያልተዋሃደዉን ክርስቶስ ብቻ ማመኑ አይደለም።
ስለዝህዮሐንስ በመሊክቱ የክርስቶስን ትምህርት ሲያጸና በ1ኛዮሐ.2፡23
ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው" ብሏል። "እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል" ስላለ የሚታየው የክርስቶስ አካል የአብም አካል እንጂ
የዎልድ ብቻ አለመሆኑን በማይሻር ትምህርቱ አረጋግጧል። ስለዚህም ነው ሃዋሪያው ጳዉሎስ በ1ኛጢሞ.3፡16እግዚአብሔርንም
የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ
የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።" በማለት አንድ እግዚአብሔር የተገለጠበት ሰዉነት(አካል) መኖሩን
ያስተመረው ። በቆላስይስ.2፡8_9እንደ ክርስቶስ ትምህርት
ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ
ተጠበቁ።በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤"
በማለት ከምልኮቱ ሙላት ምንም ሳይቀነስ በስጋ አካል(በክርስቶስ) ተገልጦ እንደሚኖር በግልጥ በ2ኛቆሮ.5፡19 እግዚአብሔር በክርስቶስ
ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።"
በማለት በመዝ.40፡6 እንደተጻፈው እግዚአብሔር ለራሱ ባዘጋጀዉና
በተገለጠበት ሥጋና ደም አለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ በዉህደት አማኑእል ሆኖ በምድር ላይ በመካከላችን በመገኘት
እንጂ አብ በሰማይ ቀርቶ ዎልድን ብቻ ወደ ምድር ልኮ አይደለም(መዝ.139)፡7_9፣ዮሐ.3፡13፣
ኢሳ59፤16፣ ኢሳ.7፡13፣ ኢሳ.9፡6፣ ኢሳ.52፡5_6)። በዮሐ.8፡24_25እንግዲህ በኃጢአታችሁ
ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው እንግዲህ። አንተ ማን ነህ?
አሉት። ኢየሱስም ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ።. . .ስለ አብ እንደነገራቸው አላስተዋሉም"ይላል።
በስጋ ከመገለጡ በፊት ለነአብርሃም፣ ለነሙሴና ለነብያት ሲናገር የነበረው ብቻዉን የነበረ
እዉነተኛ አምላክ ራሱ መሆኑን አረጋግጦ አስተምሯል። በጊዜው ለጻህፍትና ፈሪሳዊያን ይህንን ሲናገር በዮሐ.8፡27
እንደተጻፈው ስለ አብነቱ ኢንደነገራቸው አላስተዋሉም።የበለጠ ሲያረጋግጥላቸው፦ከዮሐ.8፡56_59አባታችሁ
አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።አይሁድም ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን
አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ
ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።' በዮሐ.10፡33 ላይ ክርስቶስ፦አብና ዎልድ
በዉህደት በአንድ አካል እንዳሉ ሲያስተምር ያልተዋጠላቸው፦" አይሁድም ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤
አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት። እርሱም ለተቃወሙት መልስ ሲሰጥ በዮሐ.10፡37_38እኔ
የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ
ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።" አላቸው እነዚሁ ጻህፍትና ፈሪሳውያን በማር.2፡5_7
በተሳፈው ቃል እንደምናየው ኃጢአት የማስተሰረይ ስልጣንና ችሎታ የእግዚአብሔር አብ ብቻ ሆኖ እያለ "ክርስቶስ
ሃጢአትህ ተሰረየችልህ" በማለቱ እግዚአብሔር አብ በገዛ ሥጋዉና ደሙ (በክርስቶስ) ዓጢአትን እያስተሰረየ እንዳለ
አላወቁምና ሰው ሆኖ ሳለ የአብን ሥራ፣ችሎታና ስልጣን ወሰደ ብለው አወገዙት(ሮሜ.8፡33፣2ኛቆሮ.5፡19፣
ኢሳ.43፡25፣ ኢሳ.43፡10_11፣ ኢሳ.45፡21_25፣ 1ኛጢሞ..1፡15_17፣ ቲቶ.2፡11_14፣ 1ኛዮሐ.5፡20)።
በሐ.ስራ 20፡28በገዛ ደሙ የዋጃትን
የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው
ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።" ተብሎ ስለተጻፈ በዘላለም መንፈስ ለኃጢአት ስርየት የፈሰሰው የልጁ ደም ማለት ከአብ
ከገዛ ራሱ አካል የፈሰሰ ደም መሆኑን ያረጋግጣል። በዮሐ.17፡3 ላይ ኢየሱስ ሲያስተምር"
እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት"
በማለት አንድ እውነተኛ አምላክ ብቻ እንዳለና ይህም አምላክ በሥጋና በደም የተገለጠበትን ተሉኮ አስመልክቶአል።
ይህንኑ የክርስቶስ ትምህርት ሐዋሪያው ዮሐንስ በመጀመሪያው መልእክቱ (1ኛዮሐ.5፡20_21)
የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም
በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።
ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።" በማለት ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር አብም፣ ዎልድም መሆኑንና
እርሱ ብቻ የዘላለም ሕይወት እንደሆነ በግልጥ ጽፎታል። (1ኛጢሞ.1፡15_17፣
3፡16፣ ይሁዳ.ቁ.4፣ ቁ.25፣ ሮሜ.9፡5)። ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማራቸው ትምህርቶች አንዱ፦ ኢየሱስን ያየ አብን ያየ መሆኑንና
ኢየሱስን የሚጠላ ደግሞ አብንና የኢየሱስን ተከታዮች እንደሚጠላ የሚያረጋግጥ ነው (1ኛቆሮ.16፡22፣
ማቴ.10፡22)። ዮሐ.15፡21፣23 "ዳሩ ግን የላከኝን
አያውቁምና ይህን ሁሉ ስለ ስሜ ያደርጉባችሁአል። ... እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል፣ ሌላ ሰው ያላደረገዉን
ስራ በመካከላቸው ባላደረግሁ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤... አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዉማል ጠልተዉማል"
ሲል የአብንና የዎልድን ዉህደት ያልተገነዘቡ ሁሉ ክርስቶሳዊያንን እንደሚጠሉ ያስረዳል። ዮሐ.16፡1_3" እንዳትሰናከሉ ይህን
ተናግሬአችኋለሁ። ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል
የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው" ሲል ይደመድማል። በዚህች ትራክት ዉስጥ በአጭሩ የሰፈሩትን የክርስቶስን ትምህርቶች የማይቀበል ሁሉ በመዝሙር.2፡1_7
እንደተጻፈው የአብንና የዎልድን አንድነትና ውህደት በመጻረር ማሰሪያቸዉን (ውህደታቸዉን) ለመበጠስ በከንቱ በመፍጨርጨር
ላይ ያሉ በመሆናቸው የሰላም ሰዎች አይደሉምና ተመልከትዋቸው!! የክርስቶስን ትምህርት የተቀበሉትን ብቻ ምሰሉ።
እኛ ትምህርቱን የተቀበልን ሁላችን ህብረታችን ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነዉና (1ኛዮሐ1፡1_3)
|
||||||||||||||||